Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ እና ኤም.ኢ.ኤስ.ፒ. አፍሪካ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ፤የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የሠ/መ/ቁጥር 251398

የክሱ ይዘት በአጭሩ፡- ከቻይና ሀገር ለሚያስመጣቸው ብራንዳቸው ችንት የዋጋ ግምታቸው ብር 4,899,067.12 (አራት ሚልዮን ስምንት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ስልሳ ሰባት ከ12/100) የሆኑ1,176(አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰባ ስድስት) ካርቶን የተለያዩ የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች ከቻይና ተጓጉዘው ሞጆ ደረቅ ወደብ እስኪደርሱ ድረስ ጉድለትን ጭምሮ ለሚደረስ ማንኛውም ጉዳት በመድን ፖሊስ ቁጥር GU/34/2011/2019/00114 አጠቃላይ የመድህን ሽፋን የሰጣቸው ዕቃዎች ሞጆ ደረቅ ወደብ ደርሰው ከሳሽ ከመረከቡ በፊት ዕቃዎች ገበያ ላይ በመታየታቸው ፍተሻ ተደርጎ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት እንዲፈፀም ህዳር 15 ቀን 2012 ዓ.ም ከሳሽ አቤቱታ አቅርቦ የጉምሩክ ጽ/ቤት ተወካይ፤አጓዡ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት እና የከሳሽ ማኅበር ተወካዮች በተገኙበት ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም ዕቃዎቹ የመጡበት ኮንቴነር ተከፍቶ ሲፈተሸ የዋጋ ግምታቸው ብር 1,827,753.64 (አንድ ሚልዮን ስምንት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ሶስት ከ64/100) የሆነ 171 እሽግ መጉደሉ ተረጋግጦ አጓዡ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የጎደሉ ዕቃዎችን በዝርዝር በመያዝ ወደ መጋዘኑ ማስገባቱንና ተከሳሹ ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ አጓዡ ኃላፊነት ወስዶ የጉድለት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ስላልሰጠው የካሳ ክፍያ ጥያቄውን ማስተናገድ አልችልም ማለቱን ጠቅሶ ተከሳሹ ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ በገባው የማሪን ውል መሰረት የጎደሉ ዕቃዎች ዋጋ 1,827,753.64 (አንድ ሚልዮን ስምንት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ሶስት ከ64/100) ካሳ ማስጠንቀቂያ ከደረሰው ከግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ፤ ከወጪ እና ኪሳራ ጭምር እንዲከፍለው ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article ሲሲኢሲሲ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ እና አቶ ቤልሻጽር ሀይለልዑል መ/ጽድቅ የሰ.መ.ቁ.250942
Next Article የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759
Print
5959
«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

የፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ...

0

ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ የፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች ልዑክ በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ ተካሄደ

0

ፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የጉባኤው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሠረት የተቋቋመው የፌደራል ጉባኤ የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን የመጠበቅ፣ የአሰራር መመሪያዎችን የማውጣትና የማሻሻል እንዲሁም አገራዊ የዳኝነት ሂደቱን የማጠናከር ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

1345678910Last