Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ መጣልኝ መላኩ የሰ.መ.ቁ.252953 የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ የክስ አቤቱታ፡ ከሳሽ በ2005 ዓ.ም የ40/60 የመኖሪያ ቤት መርሃ ግብር ተመዝግቤ በአሁኑ ወቅቱ ባጠቃላይ 430000 ማለትም መቶ ፐርሰንት የቆጠብኩኝ በመሆኑ በዉሉና በመመሪያዉ መሰረት ቅድሚያ ዕጣ እንዲወጣልኝ መደረግ ሲገባዉ ከመመሪያዉ ዉጭ አርባ ፐርሰንት የቆጠቡ ሰዎች ተካተዉ እጣ እንዲወጣ በመደረጉ መብቴን አጣቧል፡፡ ከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረግነዉ ዉል ቤቱን ሊያስገኝ የሚያስችል ዉል የተዋዋልንና ግዴታዬን የተወጣሁ ቢሆንም ሌሎች ተከሳሾችም በመመሪያ ቁጥር 21/2005 መሰረት የሚጠበቅባቸዉን አስተዳደራዊ ኃላፊነታቸዉን በመወጣት ቤቱን ሊያስረክቡኝ አልቻሉም፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ከ3ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረገዉ ሰነድ መሰረት ተገንብተዉ የተጠናቀቁትን ቤቶች ከቢሮዉ ተረክቦ በዉሉ መሰረት ቅድሚያ ማስረከብ ሲገባዉ ይህን ያላደረገ በመሆኑ፣ ሌሎች ተከሳሾችም ኃላፊነታቸዉን ያልተወጡ በመሆናቸዉ፣ በመመሪያዉና በዉሉ መሰረት ተገንብተዉ ከተጠናቀቁ ቤቶች ላይ ከአንዱ ሳይት እንዲወስድ ተከሳሾች በአንድነትና በነጠላ ኃላፊነት አለባቸዉ ተብሎ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056 Next Article ኤልያስ ዳሪ እና እነ ወ/ሮ ሰናይት አብርሃ (6) ሰዎች የሰ/መ/ቁ. 253783 Print 2616 Documents to download 252953(.pdf, 861.73 KB) - 327 download(s)
በአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋዩች አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ በአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋዩች አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ Tuesday, January 13, 2026 16 ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰው ሃብት ስራ አመራር ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ በሬጅስትራር ስር ላሉ እና ለሌሎች የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም በአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋዩች አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡ Read more
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በወንጀል ችሎት በሚታዩ ችግሮችና... በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በወንጀል ችሎት በሚታዩ ችግሮችና... Tuesday, January 13, 2026 6 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በወንጀል ችሎቶች የሚታዩ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች ዙሪያ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ላይ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም የግብዓት ማሰባሰቢያ ዉይይት ተካሄዷል፡፡ Read more
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል... የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል... Tuesday, January 13, 2026 3 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደዉ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 81(2) መሰረት 34 የከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፡፡ Read more
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል... የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል... Tuesday, January 13, 2026 4 የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከቀን 21/04/2018 ዓ.ም እስከ 27/04/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት ጉብኝት እና ውይይት አድርገዋል፡፡ Read more
12Dec2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Friday, December 12, 2025 Read more
6Nov2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Thursday, November 6, 2025 Read more
8Oct2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Wednesday, October 8, 2025 Read more