Anonym / Monday, October 5, 2020 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation እነ አቶ አንበሳው አፈወርቅ እና አቶ አበበ ተገኝ የሠ-መ-ቁጥር 185708 ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በመጀመሪያ በታየበት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥሩ አዲስ የሆነውን በ360 ካሬ ሜትር የሰፈረ ቤት በብር 650,000.00 ከተጠሪ ገዝቻለሁ፡፡ በውሉ ላይ ተጠሪ ቤቱን እንዳስረከቡ የተገለጸ ቢሆንም ቤቱን በምረከብበት ወቅት እናቴ ከዚህ አለም በሞት የተለየች በመሆኑ ችግር ስለገጠመኝ ሳልረከብ የቀረሁ ስለሆነ ሀዘኔን ጨርሼ ተጠሪ ቤቱን እንዲያስረክቡኝ ብጠይቅም ቤቱን ሊያስረክቡኝ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ቤቱን እንዲያስረክቡኝ እና በዉሉ የተመለከተዉን መቀጫ ብር 100,000.00 እንዲከፍለኙ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም ፍሬ ነገሩን በተመለከተ በሰጡት መልስ አመልካች ከተጠሪ ጋር ፈጸምኩኝ ያሉትን ወል አልፈጸምኩም፡፡ምንም ገንዘብ አልተቀበልኩም፡፡አመልካች ፈጸምኩኝ ያሉት ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት ያልተፈጸመና ሕጋዊ መሰረት የሌለዉና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1720/1 መሰረት ረቂቅ ነዉ፡፡ ከአመልካች ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት ስለነበረኝ ጉዳይ እንዲያስፈጽሙልኝ የዉክልና ሥልጣና በርካታ ሕጋዊ ሰነዶችን ሰጥቻቸዉ በእጃቸዉ የሚገኝ ቢሆንም አመልካች ዉል አለኝ የሚሉት ዉል ሳይኖርና የተቀበልኩት ገንዘብ ሳይኖር በሀሰት የቀረበ ስለሆነ ክሱ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡…….. Previous Article በአማጋ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጮራ የጋዝና ኬሚካል ውጤቶች ፋብሪካ፣ሂክማ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ኃ/የተ/የቡድን ኢንተርፐራይዝ እና ሌሎች የሰ-መ-ቁ 175155 Next Article ወ-ሮ ገነት ገሠሰ ቸኮል እና የአ.አ ከተማ የየካ ክ-ከተማ አሰ-ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ-ቤት፣ የአ.አ ከተማ የየካ ክ-ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፅ-ቤት የሰ-መ-ቁ 180001 Print 15675 Documents to download እነ አቶ አንበሳው አፈወርቅ እና አቶ አበበ ተገኝ የሠ-መ-ቁጥር 185708(.pdf, 740.49 KB) - 1854 download(s)
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ... የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ... Monday, December 1, 2025 595 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የናሚቢያ ሪፕብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቋማዊ ግንኙነታቸውንና የዳኝነት ስርአታቸውን ማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት በቀን 20/03/2018 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡ Read more
የአፍሪካ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቶችና ጠቅላይ ፍርድ ቤት... የአፍሪካ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቶችና ጠቅላይ ፍርድ ቤት... Monday, December 1, 2025 401 4ኛውን የአፍሪካ ህገመንግሥታዊ ፍርድ ቤቶች እና መሰል ተቋማት ዓለም አቀፍ ሲምፖዝየም ‘ህገ መንግሥታዊነት እና ሀገረ መንግሥት ግንባታ’ በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ መካሄዱን ተከትሎ የመርሃግብሩ ተሳታፊ እንግዶች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 20/03/2018 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል። Read more
ለፌደራል ፍርድ ቤቶች የቤተሰብ ችሎት ዳኞች የልምድ... ለፌደራል ፍርድ ቤቶች የቤተሰብ ችሎት ዳኞች የልምድ... Monday, December 1, 2025 660 የኢንግላንድ እና ዌልስ ጠበቆች ማህበር ፕሬዚዳንት የሆኑት ክብርት ባርባራ ሚልስ በቀን 19/03/2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ለፌደራል ፍርደ ቤቶች የቤተሰብ ችሎት ዳኞች ልምዳቸውን አካፈሉ፡፡ Read more
የላይቤሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትና ልዑክ... የላይቤሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትና ልዑክ... Thursday, November 27, 2025 522 የላይቤሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ጄሚ ኩዊኪ (Honorable Jamie Quiqui Gbeisay) እና ልዑክ ቡድናቸው በቀን 17/03/2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ Read more
12Dec2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Friday, December 12, 2025 Read more
6Nov2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Thursday, November 6, 2025 Read more
8Oct2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Wednesday, October 8, 2025 Read more