Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ በላይነሽ ጫላእና አቶ ሸዋንግዛው ሽብሩ/ቁጥር የሰ/መ/ቁ 254862

ጉዳዩ በጋብቻ ዉስጥ ተፈርቷል የተባለ ሀብት ስለሚጣራበት አግባብ የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ - ከአመልካች ጋር በጋብቻ ዉስጥ በነበሩበት ጊዜ ያፈሩት ንብረቶች እንደሆነ እና ጋብቻቸዉ መፍረሱን በመግለጽ የተለያዩ ንብረቶችን በመዘርዝር ድርሻቸዉ ተካፍሎ እንዲሰጣቸዉ የጠየቁ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ በፊት አዲስ አበባ ከተማ ስር ኮዬ ፈጬ ሳይት የነበረ አሁን ላይ በሸገር ከተማ በገላን ክፍለ ከተማ ኮዬ ፈጬ ሳይት ፕሮጀክት 16፣ ብሎክ 34፣ 6ኛ ፎቅ የሚገኝ፣የቤት ቁጥር 56  ባለ ሶስት መኝታ በአመልካች ስም የተሰጠና ብር 1,500,000.00 የሚያወጣ ስላለን እኩል እንድታካፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…..

Previous Article ወ/ሮ ሳፊያ ከድር እና እነ ሐጂ አማን ሐጂ ሁሴን (6ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 254696
Next Article አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592
Print
5607

Documents to download

  • 254862(.pdf, 1.06 MB) - 715 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሬጂስራርና ችሎት አገልግሎት...

866

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሬጂስትራርና ችሎት አገልግሎት ክፍል ለተውጣጡ ሰራተኞች በሙስና ምንነት፣ በሙስና ባህሪያት፣ በአዋጅ 881/2007 የተደነገጉ የሙስና ወንጀሎች፣ የሙስና መከላከያ ስልቶች እና በሥነ ምግባር ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ በቀን 23/5/2018 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል::

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አመራሮች በፌደራል...

823

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አመራሮች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 20/05/2018 ዓ.ም በመገኘት ወደፊት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በ19ኛው የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤቶችና መሰል...

1242

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት እና የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ በሆኑት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ ወዬሳ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ማክሰኞ ጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም አልጀርስ ሲደርስ በአልጀሪያ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢኮርት ትግበራ ላይ ለፍትህ...

919

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እያከናወናቸው ካሉት ተግባራት መካከል የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ አንዱ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ከኢትዮቴሎኮም ጋር በጋራ በመሆን የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን በኔትወርክ የሚያስተሳስር የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ዝርጋታ መጠናቀቁን ተከትሎ በመሰረተ ልማቱ ላይ ተግባራዊ የሚደረጉ መተግበሪያዎችን አልምቷል፡፡

First567810121314Last