Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 5548 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 798 download(s)
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ... Friday, January 2, 2026 663 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 22/04/2018 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ አፋር ሲደርሱም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ከፍተኛ የመንግሥት ተቋማት ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ Read more
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ... የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ... Tuesday, December 30, 2025 725 የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በቀን 16/04/2018 ዓ.ም፤ በ17/04/2018 ዓ.ም እና 20/04/2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት እና ውይይት አድርገዋል፡፡ Read more
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ... ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ... Monday, December 22, 2025 463 ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባል ለነበሩት ፕሮፌሰር ሙራዱ አብዶ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 09/04/2018 ዓ.ም የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ Read more
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ... ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ... Monday, December 22, 2025 447 ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባል ለነበሩት ፕሮፌሰር ሙራዱ አብዶ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 09/04/2018 ዓ.ም የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more
12Dec2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Friday, December 12, 2025 Read more
6Nov2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Thursday, November 6, 2025 Read more
8Oct2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Wednesday, October 8, 2025 Read more