Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 የአሁን አመልካች በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ/መ/ቁ 47863 እና በመ/ቁ በመ/ቁ 47862 በሁለቱም መዝገቦች ላይ 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው የክስ ይዘትም አመልካች የኢትዮጵያ የፌዴራል ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ግምቢ ቅርንጫፍ የቡና ላኪ ሸኚ ስምሪት ጣቢያ ላይ ቋሚ ሰራተኛ ሆኖ በባለሙያነት ተቀጥሮ እየሰራ እያለ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ድርጊት በመፈጸም ለራሱ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ከተማ ቀበሌ 05 በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ግምቢ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርብ የተቀሸረ ቡና ዓይነቱ እና የሰሌዳ ቁጥሩ 3-A02958 A.A በሆነ ኤፍ.ኤስ፣አር መኪና ከነጆ ከተማ ተጭኖ በፕሎምፕ ታሽጎ የቡናው ፕሎምፕ ቁጥር GM-7 በሚባል የታሸገውን በሚልክበት ጊዜ የቡናውን መጠን አጣርቶ መላክ እያለበት የተቀሸረ 129 ኩንታል ተጭኖ እያለ 100 ኩንታል በሚል እንዲሁም ከአይራ ወረዳ በሲኖ ትራክ 210 ኩንታል ቡና የተጫነ ነዉ ተብሎ የተላከዉን ተቀብሎ በቡናው የይለፍ ወረቀት ላይ ይህንኑ መጠን በማረጋገጥ የይለፍ ወረቀት ከሰጠ በኋላ በዚሁ ቀን የተጠቀሱት መኪናዎች በጊምቢ ከተማ ልዩ ስሙ ሰርጤ ኬላ ቦታ ላይ በቁጥጥር ስር ውለዉ ሲፈተሹ 29 እና 70 ኩንታል ቡና እንደቅደም ተከተላቸዉ ከህግ ውጭ ጥራት በሌለው የማዳበሪያ ከረጢት ተጨምሮ እሱ በይለፍ ወረቀት ላይ ጽፎ ከሰጠው በላይ በተጨማሪ ተጭኖ ስለተገኘ የአዋጅ 1051/2009 አንቀጽ 19/5/ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 433/2007 አንቀጽ 41(1)(ቀ) በመተላለፍ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስቦ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ወንጀል ድርጊት ፈጽሟል የሚል ነው፡፡ መልካም ምንባብ… Previous Article አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 Next Article ወ/ሮ የማርውሃ ወርቅነህ እና እነ ወ/ሮ ዓለም ወርቅነህ የሰ.መ.ቁ 242314 Print 5825 Documents to download 267231(.pdf, 1.08 MB) - 1292 download(s)
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ... በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ... Tuesday, January 13, 2026 270 በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ፖሊሲ ላይ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ምድብ ችሎት ሰራተኞች ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተካሂዷል፡፡ Read more
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች... የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች... Tuesday, January 13, 2026 540 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 24/04/2018 ዓ.ም በመገኘት የፍርድ ቤቱን የቴክኖሎጂ መሰረት ልማቶችን ጎብኝተዋል፡፡ Read more
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ... የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ... Monday, January 5, 2026 569 በዚህ ውይይት ወቅት፣ የክልላችን ፍርድ ቤቶች በICT ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በቅንጅት እና በትብብር የተጀመሩ መልካም ስራዎች አጠናክረን ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ። Read more
በፍትህ ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህጻናትን መብት በማስጠበቅ... በፍትህ ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህጻናትን መብት በማስጠበቅ... Friday, January 2, 2026 820 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ከዩኒሴፍ ኢትዮጲያ ጋር በመተባበር ከሦስቱም ፍርድ ቤቶች የተውጣጡ ዳኞች፣ የሶሻል ወርክ ምሁራን እና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ወርክሾፕ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more
12Dec2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Friday, December 12, 2025 Read more