Selam Warga / Monday, April 27, 2026 / Categories: CASSATION, Cassation ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 271726 ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁጥር 249795 ላይ “ሠራተኛዉ በተከታታይ ከ5 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ቢቀር እንኳ ከሥራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን አሠሪዉ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) ሳይሰጥ የሥራ ዉልን ለማቋረጥ እንደማይችል” ተገልጾ የተሰጠው የህግ ትርጉም ተለውጦ “የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ለ) ድንጋጌ ሠራተኛዉ በዚሁ አዋጅ ከተመለከቱ እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ዉጭ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ላይ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ዉልን ያለ ማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ይቻላል” በሚል ተተርጉሟል፡፡ Previous Article ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 244308 Print 2033 Documents to download 271726(.pdf, 281.52 KB) - 409 download(s)
ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሬጂስራርና ችሎት አገልግሎት... ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሬጂስራርና ችሎት አገልግሎት... Monday, February 9, 2026 880 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሬጂስትራርና ችሎት አገልግሎት ክፍል ለተውጣጡ ሰራተኞች በሙስና ምንነት፣ በሙስና ባህሪያት፣ በአዋጅ 881/2007 የተደነገጉ የሙስና ወንጀሎች፣ የሙስና መከላከያ ስልቶች እና በሥነ ምግባር ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ በቀን 23/5/2018 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል:: Read more
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አመራሮች በፌደራል... የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አመራሮች በፌደራል... Thursday, January 29, 2026 839 የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አመራሮች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 20/05/2018 ዓ.ም በመገኘት ወደፊት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ Read more
በ19ኛው የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤቶችና መሰል... በ19ኛው የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤቶችና መሰል... Friday, January 23, 2026 1256 የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት እና የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ በሆኑት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ ወዬሳ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ማክሰኞ ጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም አልጀርስ ሲደርስ በአልጀሪያ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢኮርት ትግበራ ላይ ለፍትህ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢኮርት ትግበራ ላይ ለፍትህ... Thursday, January 22, 2026 935 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እያከናወናቸው ካሉት ተግባራት መካከል የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ አንዱ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ከኢትዮቴሎኮም ጋር በጋራ በመሆን የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን በኔትወርክ የሚያስተሳስር የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ዝርጋታ መጠናቀቁን ተከትሎ በመሰረተ ልማቱ ላይ ተግባራዊ የሚደረጉ መተግበሪያዎችን አልምቷል፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more