Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592

ጉዳዩ የውርስ ማጣራትን የሚመለከት ሆኖ አቤቱታው በቀረበበት የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች 5ኛ ጣልቃ ገብ ፣ 2ኛ ተጠሪ የስር ተጠሪ፤1ኛ ተጠሪ የስር አመልካች፤  ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተጠሪዎች ደግሞ 3ኛ፤4ኛ እና 6ኛ ጣ/ገቦች ነበሩ፡፡ የክርክሩ አመጣጥ በአጭሩ፡- የአሁን 1ኛ ተጠሪ  ባቀረቡት አቤቱታ የሟች ባለቤታቸው ቴውድሮስ አርአያ ወላጆች የልጃቸው አያት የሆኑት ጀነራል አርአያ ዘርዓይ ጥር 25 ቀን 2003 ዓም እናቱ ወ/ሮ ሰነዳይ ሀይሌ ጥር 04 ቀን 2004 ዓም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ መሆኑን፤ባለቤታቸው ከወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆን በ29/08/2005 ዓም ወራሽነታቸውን ያረጋገጡ ቢሆንም ውርሱ ሳይጣራ መኖሪያ ቤቱን ሳይከፋፈሉ በጋራ ይዘው ሲጠቀሙበት ቆይተው ከ2006 ዓም ጀምሮ ቤቱን አከራይተው የኪራዩን ገንዘብ እኩል እየተካፈሉ መሆኑን ገልጠው ድርሻቸውን ለይተው ለማወቅና ለማረጋገጥ እንዲችሉ የውርስ ሀብት እንዲጣራ ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…..

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ጫላእና አቶ ሸዋንግዛው ሽብሩ/ቁጥር የሰ/መ/ቁ 254862
Next Article አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594
Print
3148

Documents to download

  • 255592(.pdf, 834.83 KB) - 475 download(s)

«February 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
2627282930311
2345678
9101112131415
16171819202122
2324252627281
2345678

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ...

865

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የሶማሊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቪድዮ ኮንፍረንስ፣በሶማሊኛ ቋንቋ የሚሰራ የመዝገብ አስተዳደር፣ የኢፋይሊንግ አገልግሎት እንዲሁም የቀጠሮ መከታተያ አገልግሎትን በቀን 12/02/2018 ዓ.ም የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ክቡራን ፕሬዝደንቶች ባሉበት በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ እድሳትና...

865

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የህንጻ እድሳትና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ምርቃት በቀን 11/02/2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ሱልጣን አ/ሰላም እንዲሁም የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ክቡራን ፕሬዝደንቶች ባሉበት ተካሂዷል፡፡

በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ሲመክር የቆየው ሀገር አቀፍ...

894

ለሁሉም ፍርድ ቤቶች የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በመወያየት የዳኞች ያለመከሰስ መብት በህገ- መንግስቱ ላይ በተቀመጠ መሰረት ተግባራዊ ባልተደረገባቸው ክልሎች የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር፣ሁሉም ፍርድ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጣቸዉን እንዲያዘምኑ የሚያደርግ የቴክኖሎጂ መሰረት ልማትን የሚዘረጉበት በቂ በጀት እንዲያገኙ ሁሉም ትብብር እንዲያደርግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየተወያዩ መፍትሔ ለማምጣት የጋራ አቋም ተይዟል፡፡

ኒታ (National Institute for Trial...

739

ልዑካን ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በሙግት አሰማም ሒደት (Trial advocacy) ላይ ለተከላካይ ጠበቆች ተግባር ተኮር ሥልጠና ለመስጠት ሲሆን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፍርድ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

First678911131415Last