Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947 ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ… Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243 Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Print 6967 Documents to download 259947(.pdf, 828.26 KB) - 791 download(s)
አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... Tuesday, February 17, 2026 1906 አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ ጸሐፊ II በ ቀን 06 እና 09/06/2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታን እና ከለዉጥ ስራዎች ጋር ለማስተዋወቅ የመግቢያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና... ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና... Monday, February 16, 2026 2481 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ -ሙስናና ኮሚሽን ጋር በመተባበር በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ከፍርድ ቤት ዘርፍ ለተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች የካቲት 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ... Friday, February 13, 2026 1539 የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ቢኒያም ኤሮ ናቸው፡፡ Read more
በዳኝነት ስርአቱ ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን... በዳኝነት ስርአቱ ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን... Wednesday, February 11, 2026 1240 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በዳኝነት ስርአት ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን ለማጎልበት ከአጋር ድርጅቶች ጋር የጋራ ውይይት መድረክ በቀን 03/06/2018 ዓ.ም ተካሂዷል። Read more