Selam Warga / Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594 ጉዳዩ የዋስትና መብት አተገባበር የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረተዉ ክስ አመልካች በኢፌዲሪ ወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1/ሀ) እና 590(1/ሀ እና 2/ሐ) ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነት በሚፈፀም የሰው ማገት(መጥለፍ) ወንጀል በመፈጸሙ ተከሷል የሚል ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ አመልካች የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ፍርድ ቤቱም የዋስትና መብት ጥያቄውን በተመለከተ በሰጠው ትዕዛዝ አመልካች የተከሰሰበት ክስ በመርህ ደረጃ ዋስትና የማያስከለክል ቢሆንም እንጂ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን ድርጊት አፈፃፀም በተመለከተ አመልካች የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ ለብሰው እና የጦር መሳሪያ ይዘው ፈፀመ ተብሎ በክስ ዝርዝር ላይ ባይገለፅም ድርጊቱን ፈፅሞ ከሆነ ተሳትፎዉ ወደ ፊት ማስረጃ በመስማት ጊዜ የሚታይ ሆኖ በአጠቃላይ ከክሱ ዝርዝር ፍርድ ቤቱ የወንጀሉ አፈፃፀሙ ከባድ ሆኖ ስለአገኘዉ አመልካች ምን አልባት ወደፊት የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙ ተረጋግጦ ጥፋተኛ የሚባል ከሆነ ሊጣልበት የሚችለው ቅጣት ከባድ ሊባል የሚችል በመሆኑ ይህን ፈርቶ ቀጠሮ አክብሮ ይመጣል የሚል እምነት የለንም በማለት የአመልካችን የዋስትና መብት ጥያቄ ዉድቅ አድርጓል፡፡መልካም ንባብ….. Previous Article አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592 Next Article አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233 Print 5402 Documents to download 273594(.pdf, 1.05 MB) - 857 download(s)
ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ሲሰጥ የነበረዉ... ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ሲሰጥ የነበረዉ... Tuesday, January 13, 2026 794 በፌዴራል ህግና ፍትህ ጥናት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ከታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 4 ሳምንታት በተግባር ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል፡፡ Read more
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ... በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ... Tuesday, January 13, 2026 403 በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ፖሊሲ ላይ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ምድብ ችሎት ሰራተኞች ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተካሂዷል፡፡ Read more
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች... የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች... Tuesday, January 13, 2026 860 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 24/04/2018 ዓ.ም በመገኘት የፍርድ ቤቱን የቴክኖሎጂ መሰረት ልማቶችን ጎብኝተዋል፡፡ Read more
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ... የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ... Monday, January 5, 2026 804 በዚህ ውይይት ወቅት፣ የክልላችን ፍርድ ቤቶች በICT ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በቅንጅት እና በትብብር የተጀመሩ መልካም ስራዎች አጠናክረን ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more