Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056

ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በወረዳዉ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ የአመልካች አዉራሽ ሟች አቶ ይልማ ወልደአብና ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር ላይ በተጠቀሱት ተጠሪዎችና በአመልካች አባት በሟች አቶ ይልማ ወልደአብ ላይ ባቀረቡት ክስ በክሱ ላይ አዋሳኞቹ የተመለከተዉን 400 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈዉን  የመኖሪያ ቤት ከነሰርቪስ  ቤቶቹ ጭምር የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ/ም በተፈረመ የሽያጭ ዉል ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች (ከሥር 1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች) በብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ገዝተዉ ካርታ በስማቸዉ የተሰጣቸዉ ቢሆንም በይዞታዉ ላይ ካሉ ቤቶች መካከል አንዱን የአመልካች ወላጅ አባት (የሥር 4ኛ ተከሳሽ) ይዘዉ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸዉን ገልፀዉ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች (የሥር 1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች) የሸጡላቸዉን ቤት ከአመልካች አባት (የሥር 4ኛ ተከሳሽ) አስለቅቀዉ እንዲያስረክቡና የአመልካች አባትም (የሥር 4ኛ ተከሳሽም) መብት ሳይኖራቸዉ የያዙትን የ1ኛ ተጠሪን (የሥር ከሳሽን) ቤት ለቀዉ እንዲወጡ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት በመጠየቅ ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759
Next Article የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ መጣልኝ መላኩ የሰ.መ.ቁ.252953
Print
1827

Documents to download

  • 252056(.pdf, 838.15 KB) - 258 download(s)

«November 2025»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
1234567

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ...

517

በውይይታቸውም አፍሪካ ተኮር የሆኑ አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎችን በውጤታማነት ለመተግበር ፍርድ ቤቶች ያላቸውን ወሳኝ ሚና እና በአህጉር ደረጃ በተቋቋመው የአፍሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቶች አማራጭ የሙግት መፍቻ መድረክ (African Chief Justices ADR Forum) ኢትዮጵያ በአባልነት መሳተፍ በምትችልበት ሁኔታ እንዲሁም በሌሎች የዳኝነት ስርዓት ማሻሻያ ስራዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ዘዴ አቤቱታ...

684

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ዘዴ አቤቱታ አቀራረብ፣ ሙግት ማከናወን እና የሪከርድ አሰራር እና አስተዳደር መመሪያ ረቂቅ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የፌደራል መጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች እንዲሁም ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ በቀን 22/09/2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች የ2017 በጀት ዓመት...

1065

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና ክቡራን ዳኞች በተገኙበት ተደርጓል።

First7891012141516Last