Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947 ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ… Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243 Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Print 5375 Documents to download 259947(.pdf, 828.26 KB) - 684 download(s)
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች... የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች... Tuesday, January 13, 2026 665 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 24/04/2018 ዓ.ም በመገኘት የፍርድ ቤቱን የቴክኖሎጂ መሰረት ልማቶችን ጎብኝተዋል፡፡ Read more
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ... የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ... Monday, January 5, 2026 594 በዚህ ውይይት ወቅት፣ የክልላችን ፍርድ ቤቶች በICT ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በቅንጅት እና በትብብር የተጀመሩ መልካም ስራዎች አጠናክረን ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ። Read more
በፍትህ ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህጻናትን መብት በማስጠበቅ... በፍትህ ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህጻናትን መብት በማስጠበቅ... Friday, January 2, 2026 954 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ከዩኒሴፍ ኢትዮጲያ ጋር በመተባበር ከሦስቱም ፍርድ ቤቶች የተውጣጡ ዳኞች፣ የሶሻል ወርክ ምሁራን እና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ወርክሾፕ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ... Friday, January 2, 2026 847 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 22/04/2018 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ አፋር ሲደርሱም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ከፍተኛ የመንግሥት ተቋማት ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more