Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለአመልካች በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/2 በ4/11/2015ዓ.ም በተጻፈ በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/1 በ9/10/2015 በተጻፈ የምደባ ደብዳቤ ላይ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ውስጥ በደረጃ XVIII በመደብ ማስታወቂያ ቁጥር 13/ግብ-1094 የስራ መደብ መጠሪያ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው መመደባቸውን በመግለጽ ሆኖም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞች ምደባ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ከአመልካች ጋር የተወዳደሩት ተወዳዳሪው የትምህርት ደረጃ በዲፕሎማ የእንስሳት እርባታ (Animal Production and Rangeland management) ይዘው የልማት ጣቢያ ሰራተኛ ሆነው የሰሩት የስራ ልምድ አያያዝ ትክክል አይደለም በማለት ባቀረቡት ቅሬታ ላይ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው ቅሬታው ተገቢ መሆኑን ተገንዝቦ ምደባው እንዲስተካከል በወሰኑት ውሳኔ መሰረት አመልካች የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተመደቡበት የስራ ምደባ ከሀምሌ 1 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ተነስቷል በማለት በጻፈው ደብዳቤ ያሳለፈውን ውሳኔ አመልካች በመቃወም ለየኢፌዲሪ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳደር ፍርድቤት ባቀረቡት ይግባኝ ያለኝ ዲፕሎማ እንስሳት እርባታ (Animal Production and RangeLand Management) ቢሆንም የተቀጠርኩት እና ለ6 አመት ያገለገልኩት ግን ሁሉንም የግብርና ሙያ ድጋፍ ማድረግ የሚችል አጠቃላይ እርሻ ዲፕሎማ ሙያ በሚጠይቀው ማለትም 2ኛ እና 1ኛ ደረጃ ሁለገብ ልማት ጣቢያ ሰራተኛ እንደቅደም ተከተሉ ነው፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947 Next Article አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 Print 3745 Documents to download 260594(.pdf, 874.35 KB) - 506 download(s)
18ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በፌደራል ጠቅላይ... 18ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በፌደራል ጠቅላይ... Monday, October 13, 2025 863 በአገር አቀፍ ደረጃ "ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!" በሚል መሪ ቃል 18ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ሥነሥርዓት ተከብሯል፡፡ Read more
ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ Monday, October 13, 2025 1132 ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች "Building the power of trust and enhancing judicial integrity" እና "The role of technology in building judicial trust and enhancing accessibility" በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከቀን 01-02/02/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የቆየ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ... የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ... Monday, October 13, 2025 959 የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ፣የፌደራል ፍርድ ቤት አመራሮች፣ክቡራን ዳኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂደል፡፡ Read more
በሶማሌ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት... በሶማሌ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት... Tuesday, September 9, 2025 818 ልዑክ ቡድኑ በነበረው ቆይታም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተከናወኑ ያሉ በርካታ የለውጥ ተግባራትና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት አፈጻጸሞች እንዲሁም አተገባበር ምን እንደሚመስል በቀን 04/13/2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ምልከታ እና ውይይት አካሂዷል ፡፡ Read more
12Dec2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Friday, December 12, 2025 Read more
6Nov2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Thursday, November 6, 2025 Read more
8Oct2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Wednesday, October 8, 2025 Read more