Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ሐረማያ ዩንቨርስቲ እና መላ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግል ማሕበር የሰ/መ/ቁ. 253530

ጉዳዩ ከግንባታ ውል ጋር በተያያዘ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ በቀረበው የዳኝነት ጥያቄ መሰረት መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበርአቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ተከሳሽ ነበር፡፡አመልካች በ20/01/2013 ዓ/ም ጽፎ ባቀረበው ክስ አመልካች እና ተጠሪ በነሀሴ 2009ዓ/ም እ.ኤ.አ የማስፋፊያ ግንባታ ለማከናወን ተስማምተው ተጠሪ ሳይቱን በመረከብ የግንባታ ማስፋፊያ ስራውን ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በውሉ በተቀመጠው ጊዜ እና ጥራት የግንባታ ስራውን ማከናወን ባለመቻሉ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቅያ ሰጥቶ ስራው 93% ላይ እያለ አመልካች ውሉን አቋርጧል፡፡ በመሆኑም ለአምስት ሕንፃዎች/ብሎኮች የስራ ግድፈት ማስተካከያ ብር 2,031,357.91፣ ለኩሽና፣ መጽሀፍት ቤትና ምግብ ቤት ማስተካከያ ሥራ ብር 350,759.30፣ የውሉ አፈጻጸም በመዝግየቱ በውሉ አንቀጽ 49.1 መሰረት የጠቅላላ ውሉን ዋጋ 10% የደረሰ ኪሣራ ብር 5,219,807.91እና የቀሪ ሥራ ማጠናቀቂያ ብር 492,255.18በድምሩ ብር 10,107,964.5 ተጠሪ እንዲከፍል እንዲወሰንለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…..

Previous Article አቶ ቴዎድሮስ መስፋን ህንፃ ሥራ ተቋራጭእና አዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (በአሁኑ - የአ/አ ቤ/ልማት ኮርፖሬሽን) የሰበር መ/ቁ 253303
Next Article ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ኃይሉ እና እነ ወ/ሮ እታገኘው ኃይሉ(4ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 253718
Print
5107

Documents to download

  • 253530(.pdf, 849.38 KB) - 687 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

በፍትህ ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህጻናትን መብት በማስጠበቅ...

1242

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ከዩኒሴፍ ኢትዮጲያ ጋር በመተባበር ከሦስቱም ፍርድ ቤቶች የተውጣጡ ዳኞች፣ የሶሻል ወርክ ምሁራን እና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ወርክሾፕ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ...

1118

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 22/04/2018 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

አፋር ሲደርሱም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ከፍተኛ የመንግሥት ተቋማት ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ...

1007

ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባል ለነበሩት ፕሮፌሰር ሙራዱ አብዶ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 09/04/2018 ዓ.ም የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

First89101113151617Last