Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947 ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ… Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243 Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Print 6216 Documents to download 259947(.pdf, 828.26 KB) - 754 download(s)
በፍትህ ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህጻናትን መብት በማስጠበቅ... በፍትህ ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህጻናትን መብት በማስጠበቅ... Friday, January 2, 2026 1237 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ከዩኒሴፍ ኢትዮጲያ ጋር በመተባበር ከሦስቱም ፍርድ ቤቶች የተውጣጡ ዳኞች፣ የሶሻል ወርክ ምሁራን እና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ወርክሾፕ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ... Friday, January 2, 2026 1113 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 22/04/2018 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ አፋር ሲደርሱም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ከፍተኛ የመንግሥት ተቋማት ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ Read more
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ... የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ... Tuesday, December 30, 2025 1241 የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በቀን 16/04/2018 ዓ.ም፤ በ17/04/2018 ዓ.ም እና 20/04/2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት እና ውይይት አድርገዋል፡፡ Read more
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ... ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ... Monday, December 22, 2025 1002 ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባል ለነበሩት ፕሮፌሰር ሙራዱ አብዶ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 09/04/2018 ዓ.ም የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more