Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ኩማ መልኩ እና አቶ ሰለሞን ዘለቀ የሰበር መ/ቁ/250546

መዝገቡ ለሰበር ችሎት የቀረበዉ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የህግ ስህተት የለዉም በማለት በመ/ቁ/ 423754 ላይ በቀን 11/09/2015ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል በዚህ ሰበር ችሎት እንዲታረም በማለት አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በስር ፍርድ ቤት አመልካቹ ከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን ጉዳዩ እርሻ መሬት ይዞታ የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካች ሃምሌ 12 ቀን 2014ዓ.ም በዲጋሉና ጢጆ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ በዲጋሉ አራቢ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘውን አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰ መሬት ከአያቴ ከበደ ዋቅጅራ እና ሴት አያቴ ወ/ሮ የሺ ተ/ማሪያም በመ/ቁ/43575 በሆነው በዉርስ ተወስኖልኝ በመ/ቁ 43575 ተፈጽሞልኝ እያለ ተጠሪ ምንም መብት ሳይኖረዉ ስለያዘብኝ እንዲለቅልኝ ሲል የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረበው መልስ ይዞታው የአመልካች አያቶች ሳይሆን በቅይይር ከአቶ ታደሰ ከበደ ያገኘሁት የግል ይዞታዬ ነው፤የተቀያየርነውን ይዞታ ሰዎች ተቀብለው የመኖሪያ ቤት የሰሩበት ሲሆን እኔም ይዞታውን እየተጠቀምኩበት ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ…..

Previous Article እነ ወ/ሮ ጌጤ ሙለታ(3ሰዎች) እና ወ/ሮ ብርሃኔ ካባ የሰ/መ/ቁ 249367
Next Article እነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ድንቁ(2ሰዎች)የቀድሞ አርጋፋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት (በአሁን አርጋፋ ማዘጋጃ ቤት)የሰ/መ/ቁ፡- 250597
Print
6147

Documents to download

  • 250546(.pdf, 1.07 MB) - 625 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ሲሰጥ የነበረዉ...

970

በፌዴራል ህግና ፍትህ ጥናት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ከታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 4 ሳምንታት በተግባር ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ...

459

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ፖሊሲ ላይ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ምድብ ችሎት ሰራተኞች ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተካሂዷል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ...

954

በዚህ ውይይት ወቅት፣ የክልላችን ፍርድ ቤቶች በICT ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በቅንጅት እና በትብብር የተጀመሩ መልካም ስራዎች አጠናክረን ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ።

First910111214161718Last