Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 8645 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1067 download(s)
በ19ኛው የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤቶችና መሰል... በ19ኛው የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤቶችና መሰል... Friday, January 23, 2026 1714 የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት እና የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ በሆኑት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ ወዬሳ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ማክሰኞ ጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም አልጀርስ ሲደርስ በአልጀሪያ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢኮርት ትግበራ ላይ ለፍትህ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢኮርት ትግበራ ላይ ለፍትህ... Thursday, January 22, 2026 1442 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እያከናወናቸው ካሉት ተግባራት መካከል የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ አንዱ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ከኢትዮቴሎኮም ጋር በጋራ በመሆን የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን በኔትወርክ የሚያስተሳስር የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ዝርጋታ መጠናቀቁን ተከትሎ በመሰረተ ልማቱ ላይ ተግባራዊ የሚደረጉ መተግበሪያዎችን አልምቷል፡፡ Read more
በአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋዩች አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ በአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋዩች አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ Tuesday, January 13, 2026 2155 ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰው ሃብት ስራ አመራር ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ በሬጅስትራር ስር ላሉ እና ለሌሎች የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም በአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋዩች አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡ Read more
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በወንጀል ችሎት በሚታዩ ችግሮችና... በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በወንጀል ችሎት በሚታዩ ችግሮችና... Tuesday, January 13, 2026 1764 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በወንጀል ችሎቶች የሚታዩ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች ዙሪያ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ላይ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም የግብዓት ማሰባሰቢያ ዉይይት ተካሄዷል፡፡ Read more