Selam Warga / Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቀበሌ 11/12/08 ሸማቾች ኃ/የተ/ሕ/ሥ/ማ እና አቶ እንኮሳ አመንቴ ሱፋ(9ሰዎች)የሰ.መ.ቁ 249104 የክሱ ይዘት በአጭሩ፡- በየካ አውራጃ ከፍተኛ 16 ቀበሌ 08 የቀድሞው የቀበሌ አመራሮች የተጠሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በማሰብ ከህብረት ሥራ ማህበር ብር 29.000 (ሃያ ዘጠኝ ሺህ ብር) በብድር መልክ ወጪ ተደርጎ ቤት እንድንገነባ ተፈቅዶልን ቤቶቹን በመገንባት የብድር ገንዘብም ተመልሷል፤ ተጠሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ነዋሪዎች በራሳችን ገንዘብ ቤቶቹን አፍርሰን እንደሰራን በወቅቱ የነበሩ የአመልካች አመራሮች አረጋግጠው በሰነድ ማስረጃ ሰጥተውናል፤ ተጠሪዎች ከ1982/1983 ጀምሮ በሰነድ አልባ በመኖሪያ ቤቶቹን ገንብተን እየኖርን እያለን ከ20 ዓመታት በኋላ አመልካች ለተጠሪዎች ያሰበ በማስመሰል ከፊሎቹን የተጠሪዎች ቤቶች ለልማት ሊፈርሱ ስለሚችሉ የጋራ መኖሪያ ቤት መንግስት እንዲሰጣችሁ እና ቀበሌው እንዲያውቃችሁ በማለት ከሱ ጋር የቤት ኪራይ ውል እንድንዋዋል ሲጠይቀን ተጠሪዎችም የአመልካች ህብረት ሥራ ማህበር አባላት በመሆናቸን እና መንግስታዊ ተቋም ነው ብለን በማመን ከ2ኛ ተጠሪ በስተቀር ከአመልካች ጋር የቤት ኪራይ ውል ልንፈርም ችለናል፤ተጠሪዎች የይዞታ ማረጋገጫ ለመቀበል በሂደት ላይ እያለን አመልካች ከህግም ሆነ ከውል የመነጨ መብት ሳይኖረው እንዳይፈጸም አድርጓል፤ አመልካች ተጠሪዎችን በማታለል ባስፈረመን የኪራይ ውል መነሻነት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኪራዩን ከፍለው ቤቱን ያስረክቡኝ በማለት ክስ አቅርቦ ተጠሪዎች ቤቱን እንድናስረክብ ተወስኗል፤ ሆኖም ከመነሻው ቦታው በጎርፍ ምክንያት ለህይወታችን እስጊ በመሆኑ ልዋጭ ቦታ እንዲሰጠን የሚመለከተውን አካል ጠይቀን ሲሰጠን በቦታው ላይ ቀበሌው ቤት መስራት ካልቻለ ነዋሪዎች በራሳችን ወጪ እንድንሰራ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በራሳችን ወጪ ቤት ገንብተን በስማችን ውሃ፣ መብራት እና መሰል መሰረታዊ አገልግሎቶችን አስገብተን የምንኖርበት ቤት በመሆኑ ቤቶቹ የተጠሪዎች ናቸው ተብሎ ይወሰንልን በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article አቶ ታዬ ከተማ ደጋጋ እናእነ አቶ ሙሉጌታ ታደሰ (3ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር---244417 Next Article እስጢፋኖስ /ዩቡና/ ዲራጎ እና የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 251519 Print 5508 Documents to download 249104(.pdf, 865.58 KB) - 588 download(s)
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል... የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል... Tuesday, January 13, 2026 2046 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደዉ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 81(2) መሰረት 34 የከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፡፡ Read more
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል... የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል... Tuesday, January 13, 2026 1945 የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከቀን 21/04/2018 ዓ.ም እስከ 27/04/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት ጉብኝት እና ውይይት አድርገዋል፡፡ Read more
ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ሲሰጥ የነበረዉ... ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ሲሰጥ የነበረዉ... Tuesday, January 13, 2026 1174 በፌዴራል ህግና ፍትህ ጥናት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ከታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 4 ሳምንታት በተግባር ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል፡፡ Read more
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ... በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ... Tuesday, January 13, 2026 583 በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ፖሊሲ ላይ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ምድብ ችሎት ሰራተኞች ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተካሂዷል፡፡ Read more