Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056 ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በወረዳዉ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ የአመልካች አዉራሽ ሟች አቶ ይልማ ወልደአብና ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር ላይ በተጠቀሱት ተጠሪዎችና በአመልካች አባት በሟች አቶ ይልማ ወልደአብ ላይ ባቀረቡት ክስ በክሱ ላይ አዋሳኞቹ የተመለከተዉን 400 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈዉን የመኖሪያ ቤት ከነሰርቪስ ቤቶቹ ጭምር የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ/ም በተፈረመ የሽያጭ ዉል ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች (ከሥር 1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች) በብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ገዝተዉ ካርታ በስማቸዉ የተሰጣቸዉ ቢሆንም በይዞታዉ ላይ ካሉ ቤቶች መካከል አንዱን የአመልካች ወላጅ አባት (የሥር 4ኛ ተከሳሽ) ይዘዉ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸዉን ገልፀዉ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች (የሥር 1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች) የሸጡላቸዉን ቤት ከአመልካች አባት (የሥር 4ኛ ተከሳሽ) አስለቅቀዉ እንዲያስረክቡና የአመልካች አባትም (የሥር 4ኛ ተከሳሽም) መብት ሳይኖራቸዉ የያዙትን የ1ኛ ተጠሪን (የሥር ከሳሽን) ቤት ለቀዉ እንዲወጡ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት በመጠየቅ ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759 Next Article የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ መጣልኝ መላኩ የሰ.መ.ቁ.252953 Print 5613 Documents to download 252056(.pdf, 838.15 KB) - 646 download(s)
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል የህግና ፍትህ... የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል የህግና ፍትህ... Friday, December 5, 2025 1534 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል የህግና ፍትህ ኢኒስቲትዩት “ትወልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር ”በሚል መሪቃል 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስናን ቀን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 25/03/2018 ዓ.ም አክብረዋል፡፡ Read more
የሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ... የሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ... Friday, December 5, 2025 1391 በሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰለሀዲን ቶፊቅ የተመራ የልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 25/03/2018 ዓ.ም በመገኘት የልምድ ልወውጥ አድርገዋል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባበሩት መንግስታት የልማት... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባበሩት መንግስታት የልማት... Wednesday, December 3, 2025 1742 የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) የፈረንጆቹ 2025 እየተገባደደ መሆኑን ተከትሎ በቀጣይ ከፍርድ ቤቱ ጋር በትብብር ስለሚሰራባቸው ሁኔታዎች ከፍርድ ቤቱ አመራሮች ጋር በቀን 23/03/2018 ዓ.ም ተወያይቷል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት... Monday, December 1, 2025 1579 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ የንብረት አገማመት መምሪያዎች/ማኑዋሎች ላይ ከቀን 20/03/2018 ዓ.ም-21/03/2018 ዓ.ም ለ2 ቀናት የቆየ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more