Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947 ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ… Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243 Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Print 6209 Documents to download 259947(.pdf, 828.26 KB) - 754 download(s)
የሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ... የሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ... Friday, December 5, 2025 1327 በሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰለሀዲን ቶፊቅ የተመራ የልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 25/03/2018 ዓ.ም በመገኘት የልምድ ልወውጥ አድርገዋል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባበሩት መንግስታት የልማት... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባበሩት መንግስታት የልማት... Wednesday, December 3, 2025 1667 የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) የፈረንጆቹ 2025 እየተገባደደ መሆኑን ተከትሎ በቀጣይ ከፍርድ ቤቱ ጋር በትብብር ስለሚሰራባቸው ሁኔታዎች ከፍርድ ቤቱ አመራሮች ጋር በቀን 23/03/2018 ዓ.ም ተወያይቷል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት... Monday, December 1, 2025 1542 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ የንብረት አገማመት መምሪያዎች/ማኑዋሎች ላይ ከቀን 20/03/2018 ዓ.ም-21/03/2018 ዓ.ም ለ2 ቀናት የቆየ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡ Read more
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ... የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ... Monday, December 1, 2025 1309 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የናሚቢያ ሪፕብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቋማዊ ግንኙነታቸውንና የዳኝነት ስርአታቸውን ማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት በቀን 20/03/2018 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more