Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 8537 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1057 download(s)
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል... የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል... Tuesday, January 13, 2026 1912 የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከቀን 21/04/2018 ዓ.ም እስከ 27/04/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት ጉብኝት እና ውይይት አድርገዋል፡፡ Read more
ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ሲሰጥ የነበረዉ... ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ሲሰጥ የነበረዉ... Tuesday, January 13, 2026 1086 በፌዴራል ህግና ፍትህ ጥናት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ከታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 4 ሳምንታት በተግባር ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል፡፡ Read more
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ... በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ... Tuesday, January 13, 2026 564 በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የትንኮሳ መካላከያ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ፖሊሲ ላይ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ምድብ ችሎት ሰራተኞች ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተካሂዷል፡፡ Read more
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች... የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች... Tuesday, January 13, 2026 1172 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 24/04/2018 ዓ.ም በመገኘት የፍርድ ቤቱን የቴክኖሎጂ መሰረት ልማቶችን ጎብኝተዋል፡፡ Read more