Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233

የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለግልግል ዳኝነት ጉባኤ በ1ኛ አመልካች ላይ ባቀረበው ክስ በተጠሪ እና በ2ኛ አመልካች(ስር ጣልቃገብ ) መካከል ከወራቤ እስከ በጆበር ያለውን 38.5ኪ.ሜ የመንገድ ስራ ፐሮጀክት ለማከናወን እ.ኤ.አ ሜይ 20 2016 ውል የተፈረመ ሲሆን የውሉም አይነት ስራ ተቋራጩ(2ኛ አመልካች) የዲዛይንና የግንባታ ስራውን በሙሉ በኃላፊነት የሚያከናውንበት ነው፡፡ በውሉ መሰረት ስራ ተቋራጩ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና የማቅረብ ግዴታ ስላለበት ይህን ተከትሎ ተቋራጩ የውሉን 10% ይኅውም ለብር 45‚844‚565 እ.ኤ.አ ከሜይ 13 2016 ጀምሮ ለአራት አመት ጸንቶ የሚቆይ የቦንድ ፖሊሲ ቁጥሩ በተገለጸ 1ኛ አመልካች የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ሰጥቷል፡፡ በውሉ መሰረት እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 26 2017 የተጀመረው የግንባታ ስራ በ1095 ቀናት ተጠናቆ ለግዜያዊ ርክክብ ብቁ መደረግ ሲገባው እና ከአመት በኋላ ጃንዋሪ 2018 አፈጻጸሙ 30.38% መሆን ሲገባው የስራ ተቋራጩ አፈጻጸም የውሉ 8% ላይ ነበር፡፡ በዛን ግዜም ከውሉ መፈጸሚያ ግዜ 33.8% ባክኖ ነበር፡፡ ተጠሪ ለስራ ተቋራጩ በቂ የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ቢሰጠውም፤ ሶስት የክፍያ ሰርተፍኬቶችም ጸድቀው ገንዘብ ቢከፈለውም፤ የውል ግዴታውን እንዲወጣ ተጠሪና የፕሮጀክቱ አማካሪ ድርጅት ተደጋጋሚ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ ቢሰጡትም ይህን ባለመቀበል የግንባታ ቦታውን ጥሎ በመሄድ አይነተኛና መሰረታዊ የውል ጥሰት በመፈጸሙ ተጠሪ በውሉ መሰረት እ.ኤ.አ በ1/3/18 በተጻፈ ደብዳቤ የ2ኛ አመልካችን(ስራ ተቋራጭ) የስራ ውል አቋርጧል፡፡

የስራ ውል መቋረጡን ተከትሎ 1ኛ አመልካች የዋስትናውን ገንዘብ ገቢ እንዲያደርግ ተጠሪ ቢጠይቀውም የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ የዋስትና ግዴታውን ለመወጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ 1ኛ አመልካች በመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና መሰረት ብር 45‚844‚565 ክፍያ እንዲፈጽም ከተጠየቀበት ግዜ ከ27/6/2010ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፍል እንዲወሰንበት በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594
Next Article አቶ ጉዕሽ ካሳ ደሞዝ እና እነ አቶ አማኑኤል ወልደሊባኖስ ተስፋዬ የሠ/መ/ቁጥር 243564
Print
5559

Documents to download

  • 246233(.pdf, 1.05 MB) - 670 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ...

1355

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የናሚቢያ ሪፕብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቋማዊ ግንኙነታቸውንና የዳኝነት ስርአታቸውን ማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት በቀን 20/03/2018 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡

የአፍሪካ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቶችና ጠቅላይ ፍርድ ቤት...

967

4ኛውን የአፍሪካ ህገመንግሥታዊ ፍርድ ቤቶች እና መሰል ተቋማት ዓለም አቀፍ ሲምፖዝየም ‘ህገ መንግሥታዊነት እና ሀገረ መንግሥት ግንባታ’ በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ መካሄዱን ተከትሎ የመርሃግብሩ ተሳታፊ እንግዶች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 20/03/2018 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

ለፌደራል ፍርድ ቤቶች የቤተሰብ ችሎት ዳኞች የልምድ...

1346

የኢንግላንድ እና ዌልስ ጠበቆች ማህበር ፕሬዚዳንት የሆኑት ክብርት ባርባራ ሚልስ በቀን 19/03/2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ለፌደራል ፍርደ ቤቶች የቤተሰብ ችሎት ዳኞች ልምዳቸውን አካፈሉ፡፡

የላይቤሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትና ልዑክ...

1115

የላይቤሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ጄሚ ኩዊኪ (Honorable Jamie Quiqui Gbeisay) እና ልዑክ ቡድናቸው በቀን 17/03/2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

First1112131416181920Last