Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594

የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለአመልካች በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/2 በ4/11/2015ዓ.ም በተጻፈ በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/1 በ9/10/2015 በተጻፈ የምደባ ደብዳቤ ላይ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ውስጥ በደረጃ XVIII በመደብ ማስታወቂያ ቁጥር 13/ግብ-1094 የስራ መደብ መጠሪያ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው መመደባቸውን በመግለጽ ሆኖም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞች ምደባ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ከአመልካች ጋር የተወዳደሩት ተወዳዳሪው የትምህርት ደረጃ በዲፕሎማ የእንስሳት እርባታ (Animal Production and Rangeland management) ይዘው የልማት ጣቢያ ሰራተኛ ሆነው የሰሩት የስራ ልምድ አያያዝ ትክክል አይደለም በማለት ባቀረቡት ቅሬታ ላይ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው ቅሬታው ተገቢ መሆኑን ተገንዝቦ ምደባው እንዲስተካከል በወሰኑት ውሳኔ መሰረት አመልካች የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተመደቡበት የስራ ምደባ ከሀምሌ 1 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ተነስቷል በማለት በጻፈው ደብዳቤ ያሳለፈውን ውሳኔ አመልካች በመቃወም ለየኢፌዲሪ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳደር ፍርድቤት ባቀረቡት ይግባኝ ያለኝ ዲፕሎማ እንስሳት እርባታ (Animal Production and RangeLand Management) ቢሆንም የተቀጠርኩት እና ለ6 አመት ያገለገልኩት ግን ሁሉንም የግብርና ሙያ ድጋፍ ማድረግ የሚችል አጠቃላይ እርሻ ዲፕሎማ ሙያ በሚጠይቀው ማለትም 2ኛ እና 1ኛ ደረጃ ሁለገብ ልማት ጣቢያ ሰራተኛ እንደቅደም ተከተሉ ነው፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947
Next Article አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395
Print
5079

Documents to download

  • 260594(.pdf, 874.35 KB) - 631 download(s)

«April 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
303112345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930123
45678910

ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

1649

ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች "Building the power of trust and enhancing judicial integrity" እና "The role of technology in building judicial trust and enhancing accessibility" በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከቀን 01-02/02/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የቆየ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ...

1476

የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ፣የፌደራል ፍርድ ቤት አመራሮች፣ክቡራን ዳኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂደል፡፡

በሶማሌ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት...

1251

ልዑክ ቡድኑ በነበረው ቆይታም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተከናወኑ ያሉ በርካታ የለውጥ ተግባራትና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት አፈጻጸሞች እንዲሁም አተገባበር ምን እንደሚመስል በቀን 04/13/2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ምልከታ እና ውይይት አካሂዷል ፡፡  

በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቆይታ ያደረጉ የፌደራል ጠቅላይ...

1178

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ የተመራ የዳኞች ልዑክ ቡድን "የተቀናጀ የጉዳዮች ማኔጅመንት ሲስተም እና የኤሌክትሮኒክ ሪከርድ ማኔጅመንት"(Integrated Case Management System and Electronic Record Management) ላይ ኬንያ በመገኘት ያገኘውን ልምድ በቀን 02/13/2017 ዓ.ም ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አካፍለዋል፡፡

First1112131416181920Last