Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 8048 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1020 download(s)
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ... ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ... Monday, December 22, 2025 1211 ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባል ለነበሩት ፕሮፌሰር ሙራዱ አብዶ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 09/04/2018 ዓ.ም የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ Read more
ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሬጅስትራሮች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሬጅስትራሮች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል Monday, December 15, 2025 2492 ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሬጅስትራሮች ለሬጅስትራሮች በተዘጋጀ የሥልጠና ሞጁልና ሞጁሉ ከተዘጋጀ በኋላ በወጡ ሕጎች እና በአሰራር የሚታዩ ክፍተቶችንን መሰረት ያደረገ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ Read more
ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን በተመለከተ ለተከላካይ... ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን በተመለከተ ለተከላካይ... Monday, December 8, 2025 1562 በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ከህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት የቆየ ተከታታይ ስልጠና ለተከላካይ ጠበቆች ሰጥቷል፡፡ Read more
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል የህግና ፍትህ... የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል የህግና ፍትህ... Friday, December 5, 2025 1793 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል የህግና ፍትህ ኢኒስቲትዩት “ትወልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር ”በሚል መሪቃል 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስናን ቀን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 25/03/2018 ዓ.ም አክብረዋል፡፡ Read more