Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ኩማ መልኩ እና አቶ ሰለሞን ዘለቀ የሰበር መ/ቁ/250546

መዝገቡ ለሰበር ችሎት የቀረበዉ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የህግ ስህተት የለዉም በማለት በመ/ቁ/ 423754 ላይ በቀን 11/09/2015ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል በዚህ ሰበር ችሎት እንዲታረም በማለት አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በስር ፍርድ ቤት አመልካቹ ከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን ጉዳዩ እርሻ መሬት ይዞታ የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካች ሃምሌ 12 ቀን 2014ዓ.ም በዲጋሉና ጢጆ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ በዲጋሉ አራቢ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘውን አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰ መሬት ከአያቴ ከበደ ዋቅጅራ እና ሴት አያቴ ወ/ሮ የሺ ተ/ማሪያም በመ/ቁ/43575 በሆነው በዉርስ ተወስኖልኝ በመ/ቁ 43575 ተፈጽሞልኝ እያለ ተጠሪ ምንም መብት ሳይኖረዉ ስለያዘብኝ እንዲለቅልኝ ሲል የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረበው መልስ ይዞታው የአመልካች አያቶች ሳይሆን በቅይይር ከአቶ ታደሰ ከበደ ያገኘሁት የግል ይዞታዬ ነው፤የተቀያየርነውን ይዞታ ሰዎች ተቀብለው የመኖሪያ ቤት የሰሩበት ሲሆን እኔም ይዞታውን እየተጠቀምኩበት ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ…..

Previous Article እነ ወ/ሮ ጌጤ ሙለታ(3ሰዎች) እና ወ/ሮ ብርሃኔ ካባ የሰ/መ/ቁ 249367
Next Article እነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ድንቁ(2ሰዎች)የቀድሞ አርጋፋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት (በአሁን አርጋፋ ማዘጋጃ ቤት)የሰ/መ/ቁ፡- 250597
Print
4069

Documents to download

  • 250546(.pdf, 1.07 MB) - 472 download(s)

«April 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
303112345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930123
45678910

ወጥነትና ተገማችነት በሌላቸው የሰበር ውሳኔዎች እና...

1150

ወጥነትና ተገማችነት በሌላቸው የሰበር ውሳኔዎች እና የወደፊት አቅጣጫ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በቀን 01/13/2017 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮችና ዳኞች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

የቪድዮ ኮንፍረንስ፣ ኢ- ፋይሊንግ እና ዳታቤዝ አገልግሎት...

1253

የቪድዮ ኮንፍረንስ፣ ኢ- ፋይሊንግ እና ዳታቤዝ አገልግሎት በደቡብ ምዕራብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤ፣ ቦንጋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲሁም በዞን ፍርድ ቤቶች በአጠቃላይ በ35 ፍርድ ቤቶች በቀን 30/12/2017 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል፡፡

የፍርድ ቤቶች ዲጅታላይዜሽን እና አዲሱን መመሪያ...

1237

ፌዴራል ፍ/ቤቶችን በራሳቸዉ ኔትወርክ የማስተሳሰር እና አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ መሰረት ይሆን ዘንድ ላለፉት ዓመታት ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እያስገነባ የነበረዉ ክላዉድ የመረጃ ቋት ያለዉ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተጠናቀቀ ይገኛል።

First1213141517192021Last