Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594

የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለአመልካች በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/2 በ4/11/2015ዓ.ም በተጻፈ በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/1 በ9/10/2015 በተጻፈ የምደባ ደብዳቤ ላይ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ውስጥ በደረጃ XVIII በመደብ ማስታወቂያ ቁጥር 13/ግብ-1094 የስራ መደብ መጠሪያ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው መመደባቸውን በመግለጽ ሆኖም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞች ምደባ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ከአመልካች ጋር የተወዳደሩት ተወዳዳሪው የትምህርት ደረጃ በዲፕሎማ የእንስሳት እርባታ (Animal Production and Rangeland management) ይዘው የልማት ጣቢያ ሰራተኛ ሆነው የሰሩት የስራ ልምድ አያያዝ ትክክል አይደለም በማለት ባቀረቡት ቅሬታ ላይ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው ቅሬታው ተገቢ መሆኑን ተገንዝቦ ምደባው እንዲስተካከል በወሰኑት ውሳኔ መሰረት አመልካች የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተመደቡበት የስራ ምደባ ከሀምሌ 1 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ተነስቷል በማለት በጻፈው ደብዳቤ ያሳለፈውን ውሳኔ አመልካች በመቃወም ለየኢፌዲሪ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳደር ፍርድቤት ባቀረቡት ይግባኝ ያለኝ ዲፕሎማ እንስሳት እርባታ (Animal Production and RangeLand Management) ቢሆንም የተቀጠርኩት እና ለ6 አመት ያገለገልኩት ግን ሁሉንም የግብርና ሙያ ድጋፍ ማድረግ የሚችል አጠቃላይ እርሻ ዲፕሎማ ሙያ በሚጠይቀው ማለትም 2ኛ እና 1ኛ ደረጃ ሁለገብ ልማት ጣቢያ ሰራተኛ እንደቅደም ተከተሉ ነው፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947
Next Article አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395
Print
3745

Documents to download

  • 260594(.pdf, 874.35 KB) - 506 download(s)

«February 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
2627282930311
2345678
9101112131415
16171819202122
2324252627281
2345678

የሰበር ሰርዓትን ማጠናከር ለዳኝነት ሪፎርም በሚል የቀረበ...

893

የሰበር ሰርዓትን ማጠናከር ለዳኝነት ሪፎርም(Strengthening the cassation system for effective judicial reform) በሚል የቀረበ ጽሁፍ ላይ በቀን 27/11/2017 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡

ለኢትዮጵያ አይነስውራን ብሔራዊ ማሕበር ጽ/ቤት የሰበር...

732

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሕትመት ተዘጋጅተው ከቅጽ 19-26 የወጡ የሰበር ውሳኔዎችን በድምጽ ቅጂ እንዲዘጋጁ በማድረግ ለኢትዮጵያ አይነስውራን ብሔራዊ ማሕበር ጽ/ቤት ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም አበረከተ፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ...

891

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ላደረገው አስተዋጽኦ፣ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢንፎርሜሽንና ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ሃላፊና ባለሙያዎች ላደረጉት ድጋፍ የእውቅና ምስክር ወረቀት አበርክቷል፡፡

First1213141517192021Last