Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
8645

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1067 download(s)

«September 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
31123456
78910111213
14151617181920
21222324252627
2829301234
567891011

ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን በተመለከተ ለተከላካይ...

1705

 በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ከህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት የቆየ ተከታታይ ስልጠና ለተከላካይ ጠበቆች ሰጥቷል፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል የህግና ፍትህ...

1921

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል የህግና ፍትህ ኢኒስቲትዩት “ትወልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር ”በሚል መሪቃል 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስናን ቀን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 25/03/2018 ዓ.ም አክብረዋል፡፡

የሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ...

1902

በሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰለሀዲን ቶፊቅ የተመራ የልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 25/03/2018 ዓ.ም በመገኘት የልምድ ልወውጥ አድርገዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባበሩት መንግስታት የልማት...

2120

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) የፈረንጆቹ 2025 እየተገባደደ መሆኑን ተከትሎ በቀጣይ ከፍርድ ቤቱ ጋር በትብብር ስለሚሰራባቸው ሁኔታዎች ከፍርድ ቤቱ አመራሮች ጋር በቀን 23/03/2018 ዓ.ም ተወያይቷል፡፡

First1314151618202122Last