Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ኩማ መልኩ እና አቶ ሰለሞን ዘለቀ የሰበር መ/ቁ/250546

መዝገቡ ለሰበር ችሎት የቀረበዉ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የህግ ስህተት የለዉም በማለት በመ/ቁ/ 423754 ላይ በቀን 11/09/2015ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል በዚህ ሰበር ችሎት እንዲታረም በማለት አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በስር ፍርድ ቤት አመልካቹ ከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን ጉዳዩ እርሻ መሬት ይዞታ የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካች ሃምሌ 12 ቀን 2014ዓ.ም በዲጋሉና ጢጆ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ በዲጋሉ አራቢ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘውን አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰ መሬት ከአያቴ ከበደ ዋቅጅራ እና ሴት አያቴ ወ/ሮ የሺ ተ/ማሪያም በመ/ቁ/43575 በሆነው በዉርስ ተወስኖልኝ በመ/ቁ 43575 ተፈጽሞልኝ እያለ ተጠሪ ምንም መብት ሳይኖረዉ ስለያዘብኝ እንዲለቅልኝ ሲል የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረበው መልስ ይዞታው የአመልካች አያቶች ሳይሆን በቅይይር ከአቶ ታደሰ ከበደ ያገኘሁት የግል ይዞታዬ ነው፤የተቀያየርነውን ይዞታ ሰዎች ተቀብለው የመኖሪያ ቤት የሰሩበት ሲሆን እኔም ይዞታውን እየተጠቀምኩበት ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ…..

Previous Article እነ ወ/ሮ ጌጤ ሙለታ(3ሰዎች) እና ወ/ሮ ብርሃኔ ካባ የሰ/መ/ቁ 249367
Next Article እነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ድንቁ(2ሰዎች)የቀድሞ አርጋፋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት (በአሁን አርጋፋ ማዘጋጃ ቤት)የሰ/መ/ቁ፡- 250597
Print
4069

Documents to download

  • 250546(.pdf, 1.07 MB) - 472 download(s)

«April 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
303112345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930123
45678910

የተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር...

2532

የተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 በመጽሐፍ መልክ መታተሙን ተከትሎ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ ክቡራን ዳኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነሐሴ 20 ቀን 2017 ዓ.ም የእውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

የፌደራል እና የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ውዝፍ...

1243

ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩበት የክረምት ጊዜ ውዝፍ መዛግብት ማጥራትን ለመደገፍ የሚያግዝ የመግባቢያ ስምምነት (MOU) የፌደራል እና የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎውሽፕ ኢትዮጵያ ከተሰኘ አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራረሙ፡፡

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ...

1607

ከ2002 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎችን ያጠቃለለ መጽሐፍ በልዮ ዕትም ለንባብ ምቹ ሆኖ ቀርቧል።

First1415161719212223Last