Anonym / Tuesday, October 6, 2020 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation አቶ ኢሳያስ አድማሱ አለማየሁ እና ወ-ሮ አልማዝ ተድላ ደስታ የ-ሰ-መ-ቁ 183547 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ 2ኛ ፍ/ብሄር ችሎት በኮ.መ.ቁ 62214 በ13/3/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ 230102 በ28/10/11ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ7/1/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ ሟች አባቴ አቶ አድማሱ አለማየሁ በ29/10/03ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ አመልካችን ከወራሽነት የነቀለ እና የወራሽነት ድርሻ የሌለኝ ያደረገ ስለሆነ ይህ ኑዛዜ ተሰርዞ በፍ/ብ/ህ/ቁ 842(1) መሰረት ከሌሎች ወራሾች እኩል ድርሻ ያለኝ መሆኑ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሟች ህጋዊ ሚስት ስሆን ወራሽ ባልሆን ከሚስት እና ከባለቤቴ ንብረት ድርሻ ግማሹ(50%) የኔ መሆኑ እስከታወቀ ከሌሎች ወራሾች ጋር መከሰስ የሌለብኝ በመሆኑ፤ አመልካችም ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈልገው መብት እና ጥቅም ስለሌለ ክሱ በ1ኛ ተጠሪ ላይ መቅረቡ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33 መሰረት ተቀባይነት የለውም የሚል ሲሆን፤ ተጠሪዎች በጋራ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሟች አቶ አድማሱ አለማየሁ ግንቦት 29 ቀን 2003ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በአርባ ቀን መታሰቢያው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲነበብ አመልካችም በአካል ተገኝቶ የሰማ በመሆኑ ይህን ደግሞ መቃወም የሚችለው በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(2) በ15 ቀን ውስጥ ብቻ ሲሆን አመልካችም ለሽምግልና ዳኞች ይህን ያላደረገ በመሆኑ፤ በአንቀጽ 973(2)(3) መሰረትም እስከ 3 ወር ግዜ ውስጥ ያላቀረበ በመሆኑ ክሱ በፍ/ብ/ህጉ እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 244(2)(ለ) መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱም በመቃወሚያዎቹ ላይ ክሱን ከሰማ እና የግራቀኙን ምስክሮች ቃል ከሰማ በኋላ አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ ሰምተዋል ወይስ አልሰሙም? ያልሰሙ ከሆነ የአመልካች ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው ወይስ አይደለም? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ ጉዳዩን መርምሮ የአመልካች ምስክሮች በሰጡት ቃል አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ በቦታው እንዳልነበሩ እና በእለቱም አብረው መዋላቸውን ገልጸዋል ይሁን እንጂ የአመልካች እናት አመልካች የ40 ቀን መታሰቢያው ቦታ እንዲሄድ በምስክሮች በኩል ያደረጉ ቢሆንም አመልካች ግን ሳይሄድ እንደቀረ መስክረዋል፤ የተጠሪዎች ምስክሮች በበኩላቸው አመልካች የሟች አባቱ የ40 ቀን መታሰቢያ ቀን የካቲት 5 2009ዓ.ም እዛ እንደነበር ፤ የኑዛዜው ኮፒ ለአመልካች እንደተሰጠ እና ስሙም በሄኖክ አድማሱ በሚባል ተራ ቁጥር 13 ላይ የሰፈረ ነው፤ የአመልካች ስም በሄኖክ አድማሱ ስም እንደሚታወቅ ለዚህም ማሳያ የአመልካች እናት የአመልካች ስም ሄኖክ ነው ማለታቸውን 1ኛ ምስክር መስክረዋል፤ አመልካች ጠዋት 1 ሰአት ጀምሮ እዛ እንደነበር እና የኑዛዜው ድርሻ አንሶኛል ያለውም ከ1 ወር በኋላ ነው በማለት በመመስከራቸው ከግራቀኙ ምስክሮች ቃል አመልካች ኑዛዜው በሚነበብበት ወቅት ቦታው የነበረ መሆኑን የተጠሪዎች ምስክሮች ከአመልካች ምስክሮች በበለጠ እና በአሳማኝ መልኩ በመግለጻቸው የፍ/ብሄር ህግ አንቀጽ 973(2) (3) ከደነገገው አንጻር ኑዛዜው የተነበበው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲሆን የአመልካች ክስ የቀረበው በ22/12/09ዓ.ም በመሆኑ ይህም ሲቆጠር ከ15(አስራ አምስት) ቀናት በኋላ ብሎም ከ3(ሶስት) ወር በኋላ በመሆኑ ፤ አመልካችም በኑዛዜው ላይ ስማቸው እስከሰፈረ ድረስ የፍ/ብ/ህ/ቁ 939 ከደነገገው እና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 36604 እና 53223(ቅጽ 8 እና 12) ከሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች አንጻር ከኑዛዜው ተነቅያለሁ የሚባልበት አግባብ የለም ስለሆነም ክሱ በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(1) እና 244(2) (ረ) መሰረት በይርጋ ይታገዳል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፌ/ከ/ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በሰጠው ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞታል፡፡………. Previous Article ወ-ሮ ገነት ገሠሰ ቸኮል እና የአ.አ ከተማ የየካ ክ-ከተማ አሰ-ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ-ቤት፣ የአ.አ ከተማ የየካ ክ-ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፅ-ቤት የሰ-መ-ቁ 180001 Next Article አቶ ወንድማገኝ መንግስቱ ማሞ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ-መ-ቁ 191629 Print 17887 Documents to download አቶ ኢሳያስ አድማሱ አለማየሁ እና ወ-ሮ አልማዝ ተድላ ደስታ የ-ሰ-መ-ቁ 183547(.pdf, 512.98 KB) - 1428 download(s)
አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል Monday, August 10, 2026 28 አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። Read more
የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው ስለሚቆዩባቸው... የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው ስለሚቆዩባቸው... Thursday, August 6, 2026 70 በ2018 ዓ.ም በፌደራል ፍርድ ቤቶች በርካታ መልካም አፈጻጸሞች የተመዘገቡበት ዓመት ሆኖ ያለፈ ሲሆን ከመዝገብ አፈጻጸም አኳያ በዓመቱ ለ193,590 መዛግብት ዕልባት ለመስጠት በዕቅድ ተይዞ ለ190,065 መዛግብት ዕልባት በመስጠት የዓመቱ አፈጻጸም 98.2% ደርሷል። Read more
በፌደራል ፍርድ ቤቶች ተጨማሪ ስማርት ችሎቶች አገልግሎት... በፌደራል ፍርድ ቤቶች ተጨማሪ ስማርት ችሎቶች አገልግሎት... Friday, July 31, 2026 104 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአውሮፓ ህብረት ባገኘው ድጋፍ በፌደራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በሚገኙ ምድብ ችሎቶች ተጨማሪ ስማርት ችሎቶችን በዛሬው ዕለት አስመርቆ ወደ ስራ እንዲገቡ አድርጓል። Read more
"የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... "የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... Tuesday, July 21, 2026 239 የዳኝነት ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ላለፋት ዓመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየው የቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያተኮረው የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት (Wide Area Network Project) የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። Read more