Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759 አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ የወ/ህ/ቁ.539(1)(ሀ) ን ተላልፈው ሰው ለመግደል አስቀድሞ በነበረው ሀሳብ ጨካኝነቱንና ነውረኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ ወንድሙን ሟች ጀንበሩ ወንድሙን ከአሁን በፊት ሰድቦኛል እንዲሁም በሚያሽከረክረው መኪና ሊገጨኝ ሞክሯል በማለት በቂም በቀል በመነሳት ሽጉጥ ተኩሶ ማጅራቱን ሲመታው ሲወድቅ በተደጋጋሚ ሶስት ጊዜ ተኩሶ ግንባሩን በቀኝ በኩል አንገቱንና በግራ በኩል አንገቱን በመምታት የጥይት እርሳስ ጉዳት በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤የክብ ቅርፅ ያለው ጥይት እርሳስ የገባበት ቁስል በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤ሳተላይት ቅርጽ ያለው የጥይት እርሳስ የወጣበት ቁስል፤በግራ ግንባሩ የፊተኛው ክፍል ላይ የአጥንት መሰበር ጉዳት፤በራስ ቅሉ ፊተኛው የታችኛው ክፍል ላይ እንዲደርስበት፤የመበሳት ጉዳት በአንገቱ ላይ እንዲደርስበት ፤በአንጎሉ የላይኛው ሽፋን ክፍል የተሰራጨ የደም መፍሰስ እንዲሁም የአየር ባንቧው የመበለዝ ጉዳት እና በዙሪያው ከፍተኛ ደረጃ ያለው የውስጥ ደም መፍሰስ ጉዳት እንዲደርሰበት እና ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓ በዚህም ከባድ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ፈፅሟል በማለት ከሷል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ እና ኤም.ኢ.ኤስ.ፒ. አፍሪካ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ፤የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የሠ/መ/ቁጥር 251398 Next Article አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056 Print 5257 Documents to download 251759(.docx, 142.83 KB) - 633 download(s)
ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ... ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ... Monday, May 25, 2026 339 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በፍትህ ስርዓት ውስጥ የሚያገለግሉ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎችን ሚና ለማጎልበት የሚያግዝ የስልጠና ማንዋል የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ላይ የውይይት እና የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡ Read more
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን... የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን... Thursday, May 21, 2026 313 በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት በክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አጠናቋል። Read more
በመሰረታዊ የክስ መደራደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ... በመሰረታዊ የክስ መደራደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ... Wednesday, May 20, 2026 170 ከፌዴራልና ከክልል ለተውጣጡ የዳኝነትና የፍትህ አካላት አመራሮች፣ ዳኞች እንዲሁም የሕግ ባለሙያዎች በመሰረታዊ የክስ መደራደር ( Plea bargaining) ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከፔፐርዳይን ዩኒቨርሲቲ በተጋበዙ አሰልጣኞች ተሰጥቷል። Read more
የኬንያ ፍርድ ቤት ልኡክ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት... የኬንያ ፍርድ ቤት ልኡክ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት... Wednesday, May 20, 2026 699 የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት ክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው የልዑካን ቡድን፣ በኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የልምድ ልውውጥ ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more