Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056 ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በወረዳዉ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ የአመልካች አዉራሽ ሟች አቶ ይልማ ወልደአብና ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር ላይ በተጠቀሱት ተጠሪዎችና በአመልካች አባት በሟች አቶ ይልማ ወልደአብ ላይ ባቀረቡት ክስ በክሱ ላይ አዋሳኞቹ የተመለከተዉን 400 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈዉን የመኖሪያ ቤት ከነሰርቪስ ቤቶቹ ጭምር የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ/ም በተፈረመ የሽያጭ ዉል ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች (ከሥር 1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች) በብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ገዝተዉ ካርታ በስማቸዉ የተሰጣቸዉ ቢሆንም በይዞታዉ ላይ ካሉ ቤቶች መካከል አንዱን የአመልካች ወላጅ አባት (የሥር 4ኛ ተከሳሽ) ይዘዉ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸዉን ገልፀዉ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች (የሥር 1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች) የሸጡላቸዉን ቤት ከአመልካች አባት (የሥር 4ኛ ተከሳሽ) አስለቅቀዉ እንዲያስረክቡና የአመልካች አባትም (የሥር 4ኛ ተከሳሽም) መብት ሳይኖራቸዉ የያዙትን የ1ኛ ተጠሪን (የሥር ከሳሽን) ቤት ለቀዉ እንዲወጡ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት በመጠየቅ ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759 Next Article የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ መጣልኝ መላኩ የሰ.መ.ቁ.252953 Print 5915 Documents to download 252056(.pdf, 838.15 KB) - 673 download(s)
የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው ስለሚቆዩባቸው... የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው ስለሚቆዩባቸው... Thursday, August 6, 2026 56 በ2018 ዓ.ም በፌደራል ፍርድ ቤቶች በርካታ መልካም አፈጻጸሞች የተመዘገቡበት ዓመት ሆኖ ያለፈ ሲሆን ከመዝገብ አፈጻጸም አኳያ በዓመቱ ለ193,590 መዛግብት ዕልባት ለመስጠት በዕቅድ ተይዞ ለ190,065 መዛግብት ዕልባት በመስጠት የዓመቱ አፈጻጸም 98.2% ደርሷል። Read more
በፌደራል ፍርድ ቤቶች ተጨማሪ ስማርት ችሎቶች አገልግሎት... በፌደራል ፍርድ ቤቶች ተጨማሪ ስማርት ችሎቶች አገልግሎት... Friday, July 31, 2026 99 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአውሮፓ ህብረት ባገኘው ድጋፍ በፌደራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በሚገኙ ምድብ ችሎቶች ተጨማሪ ስማርት ችሎቶችን በዛሬው ዕለት አስመርቆ ወደ ስራ እንዲገቡ አድርጓል። Read more
"የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... "የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... Tuesday, July 21, 2026 230 የዳኝነት ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ላለፋት ዓመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየው የቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያተኮረው የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት (Wide Area Network Project) የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... Tuesday, June 30, 2026 539 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል። Read more