Selam Warga / Monday, April 27, 2026 / Categories: CASSATION, Cassation ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 271726 ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁጥር 249795 ላይ “ሠራተኛዉ በተከታታይ ከ5 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ቢቀር እንኳ ከሥራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን አሠሪዉ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) ሳይሰጥ የሥራ ዉልን ለማቋረጥ እንደማይችል” ተገልጾ የተሰጠው የህግ ትርጉም ተለውጦ “የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ለ) ድንጋጌ ሠራተኛዉ በዚሁ አዋጅ ከተመለከቱ እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ዉጭ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ላይ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ዉልን ያለ ማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ይቻላል” በሚል ተተርጉሟል፡፡ Previous Article ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 244308 Print 2033 Documents to download 271726(.pdf, 281.52 KB) - 409 download(s)
ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ... ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ... Monday, May 25, 2026 339 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በፍትህ ስርዓት ውስጥ የሚያገለግሉ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎችን ሚና ለማጎልበት የሚያግዝ የስልጠና ማንዋል የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ላይ የውይይት እና የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡ Read more
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን... የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን... Thursday, May 21, 2026 313 በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት በክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አጠናቋል። Read more
በመሰረታዊ የክስ መደራደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ... በመሰረታዊ የክስ መደራደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ... Wednesday, May 20, 2026 170 ከፌዴራልና ከክልል ለተውጣጡ የዳኝነትና የፍትህ አካላት አመራሮች፣ ዳኞች እንዲሁም የሕግ ባለሙያዎች በመሰረታዊ የክስ መደራደር ( Plea bargaining) ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከፔፐርዳይን ዩኒቨርሲቲ በተጋበዙ አሰልጣኞች ተሰጥቷል። Read more
የኬንያ ፍርድ ቤት ልኡክ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት... የኬንያ ፍርድ ቤት ልኡክ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት... Wednesday, May 20, 2026 699 የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት ክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው የልዑካን ቡድን፣ በኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የልምድ ልውውጥ ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more