Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947

ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት  ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ   በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ  ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ…

Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243
Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Print
4646

Documents to download

  • 259947(.pdf, 828.26 KB) - 611 download(s)

«April 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
303112345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930123
45678910

የፕላዝማ ችሎት እና ኢ- ፋይሊንግ አገልግሎት በጋንቤላ...

1267

የጋንቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የፕላዝማ ችሎት እና ኢ-ፋይሊንግ አገልግሎት በክልሉ መጀመሩን አስመልክቶ የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት በቀን 09/12/2017 ዓ.ም ዉይይት አድርገዋል፡፡

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ክብርት...

1083

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ የተመራ ልዑክ ቡድን "የተቀናጀ የጉዳዮች ማኔጅመንት ሲስተም እና የኤሌክትሮኒክ ሪከርድ ማኔጅመንት"(Integrated Case Management System and Electronic Record Management) ላይ ኬንያ በመገኘት የልምድ ልውውጥ እያደረገ ይገኛል፡፡

የሰበር ሰርዓትን ማጠናከር ለዳኝነት ሪፎርም በሚል የቀረበ...

1322

የሰበር ሰርዓትን ማጠናከር ለዳኝነት ሪፎርም(Strengthening the cassation system for effective judicial reform) በሚል የቀረበ ጽሁፍ ላይ በቀን 27/11/2017 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡

First1516171820222324Last