Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 7349 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 971 download(s)
የፍርድ ቤቶች ዲጅታላይዜሽን እና አዲሱን መመሪያ... የፍርድ ቤቶች ዲጅታላይዜሽን እና አዲሱን መመሪያ... Friday, September 5, 2025 1767 ፌዴራል ፍ/ቤቶችን በራሳቸዉ ኔትወርክ የማስተሳሰር እና አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ መሰረት ይሆን ዘንድ ላለፉት ዓመታት ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እያስገነባ የነበረዉ ክላዉድ የመረጃ ቋት ያለዉ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተጠናቀቀ ይገኛል። Read more
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት ክቡር አቶ... በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት ክቡር አቶ... Tuesday, September 2, 2025 1681 በጉብኝታቸውም የ2017 ዓ.ም በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በክልሉ ፍርድ ቤቶች የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ደምሴ ዱላቻ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ Read more
ዓመታዊ የስራ ዕቅድና አፈጻጸም እንዲሁም የሰራተኞች... ዓመታዊ የስራ ዕቅድና አፈጻጸም እንዲሁም የሰራተኞች... Monday, September 1, 2025 2157 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ዘርፍ ሠራተኞች የተሳተፉበትና በፍርድ ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የሀሳብ ልውውጥ የተደረገበት የውይይት መድረክ ነሐሴ 24 እና 25 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሔደ፡፡ Read more
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የአሰራር... የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የአሰራር... Monday, September 1, 2025 1687 የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የአሰራር ስርዓት መመሪያ ላይ የቫሊዴሽን ወርክሾፕ በቀን 24/12/2017 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት፣ የጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝደንት፣ የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች እና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more