Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 8540 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1057 download(s)
ኒታ (National Institute for Trial... ኒታ (National Institute for Trial... Wednesday, October 22, 2025 1778 ልዑካን ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በሙግት አሰማም ሒደት (Trial advocacy) ላይ ለተከላካይ ጠበቆች ተግባር ተኮር ሥልጠና ለመስጠት ሲሆን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፍርድ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ Read more
18ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በፌደራል ጠቅላይ... 18ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በፌደራል ጠቅላይ... Monday, October 13, 2025 2455 በአገር አቀፍ ደረጃ "ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!" በሚል መሪ ቃል 18ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ሥነሥርዓት ተከብሯል፡፡ Read more
ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ Monday, October 13, 2025 2615 ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች "Building the power of trust and enhancing judicial integrity" እና "The role of technology in building judicial trust and enhancing accessibility" በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከቀን 01-02/02/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የቆየ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ... የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ... Monday, October 13, 2025 2612 የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ፣የፌደራል ፍርድ ቤት አመራሮች፣ክቡራን ዳኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂደል፡፡ Read more