Selam Warga / Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594 ጉዳዩ የዋስትና መብት አተገባበር የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረተዉ ክስ አመልካች በኢፌዲሪ ወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1/ሀ) እና 590(1/ሀ እና 2/ሐ) ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነት በሚፈፀም የሰው ማገት(መጥለፍ) ወንጀል በመፈጸሙ ተከሷል የሚል ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ አመልካች የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ፍርድ ቤቱም የዋስትና መብት ጥያቄውን በተመለከተ በሰጠው ትዕዛዝ አመልካች የተከሰሰበት ክስ በመርህ ደረጃ ዋስትና የማያስከለክል ቢሆንም እንጂ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን ድርጊት አፈፃፀም በተመለከተ አመልካች የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ ለብሰው እና የጦር መሳሪያ ይዘው ፈፀመ ተብሎ በክስ ዝርዝር ላይ ባይገለፅም ድርጊቱን ፈፅሞ ከሆነ ተሳትፎዉ ወደ ፊት ማስረጃ በመስማት ጊዜ የሚታይ ሆኖ በአጠቃላይ ከክሱ ዝርዝር ፍርድ ቤቱ የወንጀሉ አፈፃፀሙ ከባድ ሆኖ ስለአገኘዉ አመልካች ምን አልባት ወደፊት የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙ ተረጋግጦ ጥፋተኛ የሚባል ከሆነ ሊጣልበት የሚችለው ቅጣት ከባድ ሊባል የሚችል በመሆኑ ይህን ፈርቶ ቀጠሮ አክብሮ ይመጣል የሚል እምነት የለንም በማለት የአመልካችን የዋስትና መብት ጥያቄ ዉድቅ አድርጓል፡፡መልካም ንባብ….. Previous Article አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592 Next Article አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233 Print 4943 Documents to download 273594(.pdf, 1.05 MB) - 790 download(s)
በምርጫ ነክ ጉዳዮች ላይ ለዳኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና... በምርጫ ነክ ጉዳዮች ላይ ለዳኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና... Monday, April 27, 2026 220 የዳኝነትና የፍትህ አካላት በምርጫ ሂደት ወቅት የሰብአዊ መብት ጥበቃን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፎች እና ተሞክሮዎች ላይ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል። Read more
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ... የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ... Monday, April 27, 2026 280 በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2018 በጀት አመት የ9 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን አዳምጦ በተሰሩት ስራዎች ላይ በርካታ ነገሮች መሻሻላቸውን ገልፆ በቀጣይ መታረም አለባቸው ያላቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል። Read more
የዳኝነት ስርዓትን ለማዘመን እየተሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ... የዳኝነት ስርዓትን ለማዘመን እየተሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ... Wednesday, April 22, 2026 263 በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር እና የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ ተወካይ ክብርት ዶ/ር አኔሊስ ቨርስቲሸል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። Read more
በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ... በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ... Thursday, April 2, 2026 258 በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር እና የአፍሪካ አንድነት ቋሚ ተወካይ የተከበሩ ሩስላን ናሲቦቭ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገኝተው በጋራ መስራት በሚቻል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more