Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ጉዕሽ ካሳ ደሞዝ እና እነ አቶ አማኑኤል ወልደሊባኖስ ተስፋዬ የሠ/መ/ቁጥር 243564

ጉዳዩ ዳግም ዳኝነት የሚታይበትን አግባብ የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው አመልካች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የዳግም ዳኝነት አቤቱታ በማቅረባቸው ሲሆን ችሎቱ ክርክሩን መርምሮ ለሰጠዉ ዉሳኔ መነሻ ያደረገዉ ተጠሪዎች ለስር ፍርድ ቤት ያቀረቡትን የሰነድ ማስረጃዎች መሆኑን፤ነገር ግን የኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ለአመልካች ድርጅት ብር 17,500,000.00 መክፈሉን ለማረጋገጥ በይግባኝ ሰሚዉ ችሎት በመ/ቁጥር 211132 እና በመ/ቁጥር 211227 ላይ ይግባኝ ያቀረቡት የአሁን ተጠሪዎች ለስ ፍርድ ቤት በማስረጃነት ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ ሐሰተኛ ስለመሆኑ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 249579 ላይ በቀን 16/10/2014 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ማረጋገጡን በመዘርዝር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥርር 6 መሠረት ዳግም ዳኝነት እንዲታይላቸዉ ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233
Next Article እነ አቶ አበራ ነጋሽ ደምሴ(6) ሰዎች እና ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኔዓለም ቤ/ክርስቲያን፤ የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት የሰበር መ/ቁ/245981
Print
4734

Documents to download

  • 243564(.pdf, 1.07 MB) - 652 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት ውድድር ተካሄደ

535

የ9ነኛው አገር አቀፍ የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት (IHL Moot Court) ውድድር የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በጦርነት ቀውስ ወቅት የሕፃናትና ትምህርት ጥበቃ በሚል ጭብጥ ተካሂዷል፡:

 

በምርጫ ነክ ጉዳዮች ላይ ለዳኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና...

443

‎የዳኝነትና የፍትህ አካላት በምርጫ ሂደት ወቅት የሰብአዊ መብት ጥበቃን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፎች እና ተሞክሮዎች ላይ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ...

530

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2018 በጀት አመት የ9 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን አዳምጦ በተሰሩት ስራዎች ላይ በርካታ ነገሮች መሻሻላቸውን ገልፆ በቀጣይ መታረም አለባቸው ያላቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል።

135678910Last