Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ መጣልኝ መላኩ የሰ.መ.ቁ.252953 የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ የክስ አቤቱታ፡ ከሳሽ በ2005 ዓ.ም የ40/60 የመኖሪያ ቤት መርሃ ግብር ተመዝግቤ በአሁኑ ወቅቱ ባጠቃላይ 430000 ማለትም መቶ ፐርሰንት የቆጠብኩኝ በመሆኑ በዉሉና በመመሪያዉ መሰረት ቅድሚያ ዕጣ እንዲወጣልኝ መደረግ ሲገባዉ ከመመሪያዉ ዉጭ አርባ ፐርሰንት የቆጠቡ ሰዎች ተካተዉ እጣ እንዲወጣ በመደረጉ መብቴን አጣቧል፡፡ ከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረግነዉ ዉል ቤቱን ሊያስገኝ የሚያስችል ዉል የተዋዋልንና ግዴታዬን የተወጣሁ ቢሆንም ሌሎች ተከሳሾችም በመመሪያ ቁጥር 21/2005 መሰረት የሚጠበቅባቸዉን አስተዳደራዊ ኃላፊነታቸዉን በመወጣት ቤቱን ሊያስረክቡኝ አልቻሉም፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ከ3ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረገዉ ሰነድ መሰረት ተገንብተዉ የተጠናቀቁትን ቤቶች ከቢሮዉ ተረክቦ በዉሉ መሰረት ቅድሚያ ማስረከብ ሲገባዉ ይህን ያላደረገ በመሆኑ፣ ሌሎች ተከሳሾችም ኃላፊነታቸዉን ያልተወጡ በመሆናቸዉ፣ በመመሪያዉና በዉሉ መሰረት ተገንብተዉ ከተጠናቀቁ ቤቶች ላይ ከአንዱ ሳይት እንዲወስድ ተከሳሾች በአንድነትና በነጠላ ኃላፊነት አለባቸዉ ተብሎ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056 Next Article ኤልያስ ዳሪ እና እነ ወ/ሮ ሰናይት አብርሃ (6) ሰዎች የሰ/መ/ቁ. 253783 Print 2616 Documents to download 252953(.pdf, 861.73 KB) - 327 download(s)
በፍትህ ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህጻናትን መብት በማስጠበቅ... በፍትህ ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህጻናትን መብት በማስጠበቅ... Friday, January 2, 2026 47 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ከዩኒሴፍ ኢትዮጲያ ጋር በመተባበር ከሦስቱም ፍርድ ቤቶች የተውጣጡ ዳኞች፣ የሶሻል ወርክ ምሁራን እና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ወርክሾፕ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ... Friday, January 2, 2026 75 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 22/04/2018 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ አፋር ሲደርሱም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ከፍተኛ የመንግሥት ተቋማት ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ Read more
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ... የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ... Tuesday, December 30, 2025 132 የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በቀን 16/04/2018 ዓ.ም፤ በ17/04/2018 ዓ.ም እና 20/04/2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት እና ውይይት አድርገዋል፡፡ Read more
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ... ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ... Monday, December 22, 2025 111 ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባል ለነበሩት ፕሮፌሰር ሙራዱ አብዶ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 09/04/2018 ዓ.ም የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ Read more
12Dec2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Friday, December 12, 2025 Read more
6Nov2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Thursday, November 6, 2025 Read more
8Oct2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Wednesday, October 8, 2025 Read more