Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594

የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለአመልካች በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/2 በ4/11/2015ዓ.ም በተጻፈ በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/1 በ9/10/2015 በተጻፈ የምደባ ደብዳቤ ላይ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ውስጥ በደረጃ XVIII በመደብ ማስታወቂያ ቁጥር 13/ግብ-1094 የስራ መደብ መጠሪያ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው መመደባቸውን በመግለጽ ሆኖም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞች ምደባ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ከአመልካች ጋር የተወዳደሩት ተወዳዳሪው የትምህርት ደረጃ በዲፕሎማ የእንስሳት እርባታ (Animal Production and Rangeland management) ይዘው የልማት ጣቢያ ሰራተኛ ሆነው የሰሩት የስራ ልምድ አያያዝ ትክክል አይደለም በማለት ባቀረቡት ቅሬታ ላይ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው ቅሬታው ተገቢ መሆኑን ተገንዝቦ ምደባው እንዲስተካከል በወሰኑት ውሳኔ መሰረት አመልካች የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተመደቡበት የስራ ምደባ ከሀምሌ 1 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ተነስቷል በማለት በጻፈው ደብዳቤ ያሳለፈውን ውሳኔ አመልካች በመቃወም ለየኢፌዲሪ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳደር ፍርድቤት ባቀረቡት ይግባኝ ያለኝ ዲፕሎማ እንስሳት እርባታ (Animal Production and RangeLand Management) ቢሆንም የተቀጠርኩት እና ለ6 አመት ያገለገልኩት ግን ሁሉንም የግብርና ሙያ ድጋፍ ማድረግ የሚችል አጠቃላይ እርሻ ዲፕሎማ ሙያ በሚጠይቀው ማለትም 2ኛ እና 1ኛ ደረጃ ሁለገብ ልማት ጣቢያ ሰራተኛ እንደቅደም ተከተሉ ነው፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947
Next Article አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395
Print
5481

Documents to download

  • 260594(.pdf, 874.35 KB) - 697 download(s)

«May 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
27282930123
45678910
11121314151617
18192021222324
25262728293031
1234567

በፍትህ ስርአቱ ውስጥ ለሚያገለግሉ የሶሻል ወርክ...

202

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የተባባሩት መንግስታት የህዝብ ፈንድ(UNFPA) የጋራ ትብብር በፍትህ ስርአት ውስጥ የሚገለግሉ የሶሻል ወርክ ባለሞያዎችን እውቀት እና ከህሎት በተሻለ ለመገንባት እየተዘጋጀ የሚገኘው የስልጠና ማኑዋል ረቂቅ ላይ የውይይት እና ግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ በቀን 12/7/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አለም አቀፉን የሴቶች ቀን አከበሩ

209

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘንድሮ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ማርች 8 በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ GIVE TO GAIN በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ "የሴቶች ድምጽ ለዕኩልነት እና ለበለጸገች ኢትዮጵያ "በሚል መሪ ቃል መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተከብሯል፡፡

135678910Last