Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 የአሁን አመልካች በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ/መ/ቁ 47863 እና በመ/ቁ በመ/ቁ 47862 በሁለቱም መዝገቦች ላይ 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው የክስ ይዘትም አመልካች የኢትዮጵያ የፌዴራል ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ግምቢ ቅርንጫፍ የቡና ላኪ ሸኚ ስምሪት ጣቢያ ላይ ቋሚ ሰራተኛ ሆኖ በባለሙያነት ተቀጥሮ እየሰራ እያለ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ድርጊት በመፈጸም ለራሱ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ከተማ ቀበሌ 05 በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ግምቢ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርብ የተቀሸረ ቡና ዓይነቱ እና የሰሌዳ ቁጥሩ 3-A02958 A.A በሆነ ኤፍ.ኤስ፣አር መኪና ከነጆ ከተማ ተጭኖ በፕሎምፕ ታሽጎ የቡናው ፕሎምፕ ቁጥር GM-7 በሚባል የታሸገውን በሚልክበት ጊዜ የቡናውን መጠን አጣርቶ መላክ እያለበት የተቀሸረ 129 ኩንታል ተጭኖ እያለ 100 ኩንታል በሚል እንዲሁም ከአይራ ወረዳ በሲኖ ትራክ 210 ኩንታል ቡና የተጫነ ነዉ ተብሎ የተላከዉን ተቀብሎ በቡናው የይለፍ ወረቀት ላይ ይህንኑ መጠን በማረጋገጥ የይለፍ ወረቀት ከሰጠ በኋላ በዚሁ ቀን የተጠቀሱት መኪናዎች በጊምቢ ከተማ ልዩ ስሙ ሰርጤ ኬላ ቦታ ላይ በቁጥጥር ስር ውለዉ ሲፈተሹ 29 እና 70 ኩንታል ቡና እንደቅደም ተከተላቸዉ ከህግ ውጭ ጥራት በሌለው የማዳበሪያ ከረጢት ተጨምሮ እሱ በይለፍ ወረቀት ላይ ጽፎ ከሰጠው በላይ በተጨማሪ ተጭኖ ስለተገኘ የአዋጅ 1051/2009 አንቀጽ 19/5/ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 433/2007 አንቀጽ 41(1)(ቀ) በመተላለፍ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስቦ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ወንጀል ድርጊት ፈጽሟል የሚል ነው፡፡ መልካም ምንባብ… Previous Article አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 Next Article ወ/ሮ የማርውሃ ወርቅነህ እና እነ ወ/ሮ ዓለም ወርቅነህ የሰ.መ.ቁ 242314 Print 6800 Documents to download 267231(.pdf, 1.08 MB) - 1404 download(s)
የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ... የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ... Wednesday, May 13, 2026 442 የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ጋር ውይይት ተካሂዷል። Read more
የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት ውድድር ተካሄደ የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት ውድድር ተካሄደ Thursday, April 30, 2026 535 የ9ነኛው አገር አቀፍ የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት (IHL Moot Court) ውድድር የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በጦርነት ቀውስ ወቅት የሕፃናትና ትምህርት ጥበቃ በሚል ጭብጥ ተካሂዷል፡: Read more
በምርጫ ነክ ጉዳዮች ላይ ለዳኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና... በምርጫ ነክ ጉዳዮች ላይ ለዳኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና... Monday, April 27, 2026 443 የዳኝነትና የፍትህ አካላት በምርጫ ሂደት ወቅት የሰብአዊ መብት ጥበቃን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፎች እና ተሞክሮዎች ላይ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል። Read more
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ... የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ... Monday, April 27, 2026 530 በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2018 በጀት አመት የ9 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን አዳምጦ በተሰሩት ስራዎች ላይ በርካታ ነገሮች መሻሻላቸውን ገልፆ በቀጣይ መታረም አለባቸው ያላቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more