Selam Warga / Friday, March 13, 2026 / Categories: CASSATION, Cassation ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 244308 ጉዳዩ በከተማ ክልል የሚገኝ መሬት ይዞታ መብት ለማስከበር የቀረበ ክስ የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ በ14/11/2013 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ስሙ ፊጋ በሚባል ሰፈር አዋሳኞቹ በክስ የተገለፀውን ግምቱ 2000 ካ.ሜ የሆነ የእርሻ መሬት ከደርግ መንግስት ጀምሮ ተገቢውን የመሬት ግብር በመክፈል ስጠቀምበት የቆየሁትን የእርሻ መሬት ለ11 ዓመት ውጭ ሀገር ቆይቼ ግንቦት 2012 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት ስመለስ ይዞታዬን እንዲያስተዳድሩልኝ ተወካይ አስቀምጬ እያለ አመልካች ምንም ህጋዊ መብት እና የውል ግንኙነት ሳይኖረው ግምቱ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ) የሆነውን ያጠርኩትን አጥር ሰኔ ወር 2011 ዓ.ም በማፍረስ ተወካዬንም ከይዞታው በማባረር ግንብ አጥር በማጠር ቤት ሰርቶ በሕገወጥ መንገድ ይዞታዬን የያዘብኝ በመሆኑ ያለፈቃዴ የገነባውን ቤትና አጥር አፍርሶ በፍ/ሕ/ቁ 1206 መሰረት ይዞታዬን ለቆ ያስረክበኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ Previous Article ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠ የህግ ትርጉም Next Article ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 271726 Print 4237 Documents to download ሰበር መዝገብ 244308 (1)(.pdf, 551.03 KB) - 938 download(s)
የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ... የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ... Wednesday, May 13, 2026 442 የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ጋር ውይይት ተካሂዷል። Read more
የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት ውድድር ተካሄደ የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት ውድድር ተካሄደ Thursday, April 30, 2026 535 የ9ነኛው አገር አቀፍ የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት (IHL Moot Court) ውድድር የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በጦርነት ቀውስ ወቅት የሕፃናትና ትምህርት ጥበቃ በሚል ጭብጥ ተካሂዷል፡: Read more
በምርጫ ነክ ጉዳዮች ላይ ለዳኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና... በምርጫ ነክ ጉዳዮች ላይ ለዳኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና... Monday, April 27, 2026 443 የዳኝነትና የፍትህ አካላት በምርጫ ሂደት ወቅት የሰብአዊ መብት ጥበቃን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፎች እና ተሞክሮዎች ላይ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል። Read more
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ... የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ... Monday, April 27, 2026 530 በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2018 በጀት አመት የ9 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን አዳምጦ በተሰሩት ስራዎች ላይ በርካታ ነገሮች መሻሻላቸውን ገልፆ በቀጣይ መታረም አለባቸው ያላቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more