Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ኩማ መልኩ እና አቶ ሰለሞን ዘለቀ የሰበር መ/ቁ/250546

መዝገቡ ለሰበር ችሎት የቀረበዉ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የህግ ስህተት የለዉም በማለት በመ/ቁ/ 423754 ላይ በቀን 11/09/2015ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል በዚህ ሰበር ችሎት እንዲታረም በማለት አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በስር ፍርድ ቤት አመልካቹ ከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን ጉዳዩ እርሻ መሬት ይዞታ የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካች ሃምሌ 12 ቀን 2014ዓ.ም በዲጋሉና ጢጆ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ በዲጋሉ አራቢ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘውን አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰ መሬት ከአያቴ ከበደ ዋቅጅራ እና ሴት አያቴ ወ/ሮ የሺ ተ/ማሪያም በመ/ቁ/43575 በሆነው በዉርስ ተወስኖልኝ በመ/ቁ 43575 ተፈጽሞልኝ እያለ ተጠሪ ምንም መብት ሳይኖረዉ ስለያዘብኝ እንዲለቅልኝ ሲል የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረበው መልስ ይዞታው የአመልካች አያቶች ሳይሆን በቅይይር ከአቶ ታደሰ ከበደ ያገኘሁት የግል ይዞታዬ ነው፤የተቀያየርነውን ይዞታ ሰዎች ተቀብለው የመኖሪያ ቤት የሰሩበት ሲሆን እኔም ይዞታውን እየተጠቀምኩበት ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ…..

Previous Article እነ ወ/ሮ ጌጤ ሙለታ(3ሰዎች) እና ወ/ሮ ብርሃኔ ካባ የሰ/መ/ቁ 249367
Next Article እነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ድንቁ(2ሰዎች)የቀድሞ አርጋፋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት (በአሁን አርጋፋ ማዘጋጃ ቤት)የሰ/መ/ቁ፡- 250597
Print
6029

Documents to download

  • 250546(.pdf, 1.07 MB) - 624 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

‎የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን...

635

በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት በክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አጠናቋል።

‎በመሰረታዊ የክስ መደራደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ...

221

ከፌዴራልና ከክልል ለተውጣጡ የዳኝነትና የፍትህ አካላት አመራሮች፣ ዳኞች እንዲሁም የሕግ ባለሙያዎች በመሰረታዊ የክስ መደራደር ( Plea bargaining) ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከፔፐርዳይን ዩኒቨርሲቲ በተጋበዙ አሰልጣኞች ተሰጥቷል።

የኬንያ ፍርድ ቤት ልኡክ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት...

1404

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት ክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው የልዑካን ቡድን፣ በኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የልምድ ልውውጥ ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል።

124678910Last