Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
8645

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1067 download(s)

«September 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
31123456
78910111213
14151617181920
21222324252627
2829301234
567891011

በፌደራል ፍርድ ቤቶች ተጨማሪ ስማርት ችሎቶች አገልግሎት...

435

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአውሮፓ ህብረት ባገኘው ድጋፍ በፌደራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በሚገኙ ምድብ ችሎቶች ተጨማሪ ስማርት ችሎቶችን በዛሬው ዕለት አስመርቆ ወደ ስራ እንዲገቡ አድርጓል።

"የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን...

441

የዳኝነት ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ላለፋት ዓመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየው የቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያተኮረው የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት (Wide Area Network Project) የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ...

679

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል...

680

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል።

124678910Last