Anonym / Tuesday, October 6, 2020 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation አቶ ኢሳያስ አድማሱ አለማየሁ እና ወ-ሮ አልማዝ ተድላ ደስታ የ-ሰ-መ-ቁ 183547 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ 2ኛ ፍ/ብሄር ችሎት በኮ.መ.ቁ 62214 በ13/3/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ 230102 በ28/10/11ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ7/1/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ ሟች አባቴ አቶ አድማሱ አለማየሁ በ29/10/03ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ አመልካችን ከወራሽነት የነቀለ እና የወራሽነት ድርሻ የሌለኝ ያደረገ ስለሆነ ይህ ኑዛዜ ተሰርዞ በፍ/ብ/ህ/ቁ 842(1) መሰረት ከሌሎች ወራሾች እኩል ድርሻ ያለኝ መሆኑ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሟች ህጋዊ ሚስት ስሆን ወራሽ ባልሆን ከሚስት እና ከባለቤቴ ንብረት ድርሻ ግማሹ(50%) የኔ መሆኑ እስከታወቀ ከሌሎች ወራሾች ጋር መከሰስ የሌለብኝ በመሆኑ፤ አመልካችም ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈልገው መብት እና ጥቅም ስለሌለ ክሱ በ1ኛ ተጠሪ ላይ መቅረቡ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33 መሰረት ተቀባይነት የለውም የሚል ሲሆን፤ ተጠሪዎች በጋራ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሟች አቶ አድማሱ አለማየሁ ግንቦት 29 ቀን 2003ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በአርባ ቀን መታሰቢያው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲነበብ አመልካችም በአካል ተገኝቶ የሰማ በመሆኑ ይህን ደግሞ መቃወም የሚችለው በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(2) በ15 ቀን ውስጥ ብቻ ሲሆን አመልካችም ለሽምግልና ዳኞች ይህን ያላደረገ በመሆኑ፤ በአንቀጽ 973(2)(3) መሰረትም እስከ 3 ወር ግዜ ውስጥ ያላቀረበ በመሆኑ ክሱ በፍ/ብ/ህጉ እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 244(2)(ለ) መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱም በመቃወሚያዎቹ ላይ ክሱን ከሰማ እና የግራቀኙን ምስክሮች ቃል ከሰማ በኋላ አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ ሰምተዋል ወይስ አልሰሙም? ያልሰሙ ከሆነ የአመልካች ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው ወይስ አይደለም? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ ጉዳዩን መርምሮ የአመልካች ምስክሮች በሰጡት ቃል አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ በቦታው እንዳልነበሩ እና በእለቱም አብረው መዋላቸውን ገልጸዋል ይሁን እንጂ የአመልካች እናት አመልካች የ40 ቀን መታሰቢያው ቦታ እንዲሄድ በምስክሮች በኩል ያደረጉ ቢሆንም አመልካች ግን ሳይሄድ እንደቀረ መስክረዋል፤ የተጠሪዎች ምስክሮች በበኩላቸው አመልካች የሟች አባቱ የ40 ቀን መታሰቢያ ቀን የካቲት 5 2009ዓ.ም እዛ እንደነበር ፤ የኑዛዜው ኮፒ ለአመልካች እንደተሰጠ እና ስሙም በሄኖክ አድማሱ በሚባል ተራ ቁጥር 13 ላይ የሰፈረ ነው፤ የአመልካች ስም በሄኖክ አድማሱ ስም እንደሚታወቅ ለዚህም ማሳያ የአመልካች እናት የአመልካች ስም ሄኖክ ነው ማለታቸውን 1ኛ ምስክር መስክረዋል፤ አመልካች ጠዋት 1 ሰአት ጀምሮ እዛ እንደነበር እና የኑዛዜው ድርሻ አንሶኛል ያለውም ከ1 ወር በኋላ ነው በማለት በመመስከራቸው ከግራቀኙ ምስክሮች ቃል አመልካች ኑዛዜው በሚነበብበት ወቅት ቦታው የነበረ መሆኑን የተጠሪዎች ምስክሮች ከአመልካች ምስክሮች በበለጠ እና በአሳማኝ መልኩ በመግለጻቸው የፍ/ብሄር ህግ አንቀጽ 973(2) (3) ከደነገገው አንጻር ኑዛዜው የተነበበው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲሆን የአመልካች ክስ የቀረበው በ22/12/09ዓ.ም በመሆኑ ይህም ሲቆጠር ከ15(አስራ አምስት) ቀናት በኋላ ብሎም ከ3(ሶስት) ወር በኋላ በመሆኑ ፤ አመልካችም በኑዛዜው ላይ ስማቸው እስከሰፈረ ድረስ የፍ/ብ/ህ/ቁ 939 ከደነገገው እና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 36604 እና 53223(ቅጽ 8 እና 12) ከሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች አንጻር ከኑዛዜው ተነቅያለሁ የሚባልበት አግባብ የለም ስለሆነም ክሱ በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(1) እና 244(2) (ረ) መሰረት በይርጋ ይታገዳል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፌ/ከ/ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በሰጠው ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞታል፡፡………. Previous Article ወ-ሮ ገነት ገሠሰ ቸኮል እና የአ.አ ከተማ የየካ ክ-ከተማ አሰ-ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ-ቤት፣ የአ.አ ከተማ የየካ ክ-ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፅ-ቤት የሰ-መ-ቁ 180001 Next Article አቶ ወንድማገኝ መንግስቱ ማሞ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ-መ-ቁ 191629 Print 17887 Documents to download አቶ ኢሳያስ አድማሱ አለማየሁ እና ወ-ሮ አልማዝ ተድላ ደስታ የ-ሰ-መ-ቁ 183547(.pdf, 512.98 KB) - 1428 download(s)
የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ... የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ... Wednesday, May 13, 2026 733 የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ጋር ውይይት ተካሂዷል። Read more
የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት ውድድር ተካሄደ የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት ውድድር ተካሄደ Thursday, April 30, 2026 920 የ9ነኛው አገር አቀፍ የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት (IHL Moot Court) ውድድር የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በጦርነት ቀውስ ወቅት የሕፃናትና ትምህርት ጥበቃ በሚል ጭብጥ ተካሂዷል፡: Read more
በምርጫ ነክ ጉዳዮች ላይ ለዳኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና... በምርጫ ነክ ጉዳዮች ላይ ለዳኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና... Monday, April 27, 2026 752 የዳኝነትና የፍትህ አካላት በምርጫ ሂደት ወቅት የሰብአዊ መብት ጥበቃን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፎች እና ተሞክሮዎች ላይ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል። Read more
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ... የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ... Monday, April 27, 2026 782 በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2018 በጀት አመት የ9 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን አዳምጦ በተሰሩት ስራዎች ላይ በርካታ ነገሮች መሻሻላቸውን ገልፆ በቀጣይ መታረም አለባቸው ያላቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል። Read more