Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ በላይነሽ ጫላእና አቶ ሸዋንግዛው ሽብሩ/ቁጥር የሰ/መ/ቁ 254862

ጉዳዩ በጋብቻ ዉስጥ ተፈርቷል የተባለ ሀብት ስለሚጣራበት አግባብ የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ - ከአመልካች ጋር በጋብቻ ዉስጥ በነበሩበት ጊዜ ያፈሩት ንብረቶች እንደሆነ እና ጋብቻቸዉ መፍረሱን በመግለጽ የተለያዩ ንብረቶችን በመዘርዝር ድርሻቸዉ ተካፍሎ እንዲሰጣቸዉ የጠየቁ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ በፊት አዲስ አበባ ከተማ ስር ኮዬ ፈጬ ሳይት የነበረ አሁን ላይ በሸገር ከተማ በገላን ክፍለ ከተማ ኮዬ ፈጬ ሳይት ፕሮጀክት 16፣ ብሎክ 34፣ 6ኛ ፎቅ የሚገኝ፣የቤት ቁጥር 56  ባለ ሶስት መኝታ በአመልካች ስም የተሰጠና ብር 1,500,000.00 የሚያወጣ ስላለን እኩል እንድታካፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…..

Previous Article ወ/ሮ ሳፊያ ከድር እና እነ ሐጂ አማን ሐጂ ሁሴን (6ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 254696
Next Article አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592
Print
5615

Documents to download

  • 254862(.pdf, 1.06 MB) - 715 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት የወንጀል...

552

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአውሮፓ ህብረት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ሁለት የስልጠና ማኑዋሎች ማለትም ተከታታይ የወንጀል ችሎት አመራር ሥልጠና ማንዋል( Training Manual on continuous criminal trials )፣ ድንበር ተሻጋሪ እና ከባድ ወንጀሎች ሥልጠና ሞጁል(Training Module on Trans-Boundary and grave crimes) እንዲሁም "በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት የወንጀል ህግ ትርጉም ውሳኔዎች ስብስብ በጉዳዮች የተደራጁ ልዩ ዕትም" መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማስተዋወቅ ፕሮግራም አካሂዷል ፡፡

በፍትህ ስርአቱ ውስጥ ለሚያገለግሉ የሶሻል ወርክ...

551

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የተባባሩት መንግስታት የህዝብ ፈንድ(UNFPA) የጋራ ትብብር በፍትህ ስርአት ውስጥ የሚገለግሉ የሶሻል ወርክ ባለሞያዎችን እውቀት እና ከህሎት በተሻለ ለመገንባት እየተዘጋጀ የሚገኘው የስልጠና ማኑዋል ረቂቅ ላይ የውይይት እና ግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ በቀን 12/7/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አለም አቀፉን የሴቶች ቀን አከበሩ

556

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘንድሮ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ማርች 8 በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ GIVE TO GAIN በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ "የሴቶች ድምጽ ለዕኩልነት እና ለበለጸገች ኢትዮጵያ "በሚል መሪ ቃል መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተከብሯል፡፡

123578910Last