Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ መጣልኝ መላኩ የሰ.መ.ቁ.252953

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ የክስ አቤቱታ፡ ከሳሽ በ2005 ዓ.ም የ40/60 የመኖሪያ ቤት መርሃ ግብር ተመዝግቤ በአሁኑ ወቅቱ ባጠቃላይ 430000 ማለትም መቶ ፐርሰንት የቆጠብኩኝ በመሆኑ በዉሉና በመመሪያዉ መሰረት ቅድሚያ ዕጣ እንዲወጣልኝ መደረግ ሲገባዉ ከመመሪያዉ ዉጭ አርባ ፐርሰንት የቆጠቡ ሰዎች ተካተዉ እጣ እንዲወጣ በመደረጉ መብቴን አጣቧል፡፡ ከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረግነዉ ዉል ቤቱን ሊያስገኝ የሚያስችል ዉል የተዋዋልንና ግዴታዬን የተወጣሁ ቢሆንም ሌሎች ተከሳሾችም በመመሪያ ቁጥር 21/2005 መሰረት የሚጠበቅባቸዉን አስተዳደራዊ ኃላፊነታቸዉን በመወጣት ቤቱን ሊያስረክቡኝ አልቻሉም፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ከ3ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረገዉ ሰነድ መሰረት ተገንብተዉ የተጠናቀቁትን ቤቶች ከቢሮዉ ተረክቦ በዉሉ መሰረት ቅድሚያ ማስረከብ ሲገባዉ ይህን ያላደረገ በመሆኑ፣ ሌሎች ተከሳሾችም ኃላፊነታቸዉን ያልተወጡ በመሆናቸዉ፣ በመመሪያዉና በዉሉ መሰረት ተገንብተዉ ከተጠናቀቁ ቤቶች ላይ ከአንዱ ሳይት እንዲወስድ ተከሳሾች በአንድነትና በነጠላ ኃላፊነት አለባቸዉ ተብሎ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056
Next Article ኤልያስ ዳሪ እና እነ ወ/ሮ ሰናይት አብርሃ (6) ሰዎች የሰ/መ/ቁ. 253783
Print
2616

Documents to download

  • 252953(.pdf, 861.73 KB) - 327 download(s)

«January 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
2930311234
567891011
12131415161718
19202122232425
2627282930311
2345678

የሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ...

314

በሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰለሀዲን ቶፊቅ የተመራ የልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 25/03/2018 ዓ.ም በመገኘት የልምድ ልወውጥ አድርገዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባበሩት መንግስታት የልማት...

582

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) የፈረንጆቹ 2025 እየተገባደደ መሆኑን ተከትሎ በቀጣይ ከፍርድ ቤቱ ጋር በትብብር ስለሚሰራባቸው ሁኔታዎች ከፍርድ ቤቱ አመራሮች ጋር በቀን 23/03/2018 ዓ.ም ተወያይቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት...

432

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ የንብረት አገማመት መምሪያዎች/ማኑዋሎች ላይ ከቀን 20/03/2018 ዓ.ም-21/03/2018 ዓ.ም ለ2 ቀናት የቆየ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ...

384

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የናሚቢያ ሪፕብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቋማዊ ግንኙነታቸውንና የዳኝነት ስርአታቸውን ማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት በቀን 20/03/2018 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡

123578910Last