Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
7392

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 972 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስራ ሃላፊዎች የፕሮጀክት...

4080

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የፍትሕ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች ከአውሮፓ ህብረት የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ማሻሻያ ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የፕሮጀክት አስተዳደር የ5 ቀን ስልጠና ወስደዋል፡፡

በህፃናት የቀለብ አወሳሰን ረቂቅ መመሪያ ላይ ዉይይት ተደረገ

2881

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ፅ/ቤት ባዘጋጀዉ የህፃናት ቀለብ አወሳሰን ረቂቅ መመሪያ ላይ የግብአት ማሰባሰብያ ዉይይት አድርጓል፡፡ 

ዜና ሹመት

5258

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ የ16 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አጸደቀ 

የካናዳ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና ጠቅላይ አቃቤ ህግ...

2580

የካናዳ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክቡር አቶ አሪፍ ቪራኒ ከልዑክ ቡድናቸው ጋር በመሆን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

First4546474850525354Last