የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የፍርድ ቤትን አሰራር ይበልጥ ለማዘመን የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ/ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ የስምምነቱ አላማ ተቋማቱ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ተያያዥ ፕሮጀክቶች ጋር በተገናኘ ዘላቂነት ያለው ትብብርና ስኬታማ የአሰራር ዘዴዎችን እንዲፈጥሩ ለማስቻል ነው።