Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
7489

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 976 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የስድስት ወር አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

4474

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የ2016 ዓ.ም የስድስት ወር አፈጻጸም ግምገማና ውይይት በቀን 09/06/2016 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ በአፈጻጸም ግምገማው የዳኞች እና አስተዳደር ሰራተኞች የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማና ውይይት የተደረገ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ የጉዳዮች ፍሰት አፈጻጸም ሪፖርት፣ የኢንስፔክሽን ግኝት ሪፖርት፣ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አይ.ሲ.ቲ ፕሮጀክቶች የተመለከተ ገለጻ እንዲሁም የህጻናት ተስማሚ ፍ/ቤቶች ረቂቅ መመሪያ ላይ ገለጻና ውይይት ተደርጓል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የአስተዳደር ሰራተኞች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ ከየስራ ክፍሎቹ የአፈጻጸም ግምገማና ውይይት በተጨማሪ የአስተዳደር ሰራተኞች ደንብ 01/2015 ላይ ገለጻ ተደርጓል፡፡ 

በኢትዮጵያ የቤልጅየም አምባሳደር የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ...

7886

በኢትዬጵያ የቤልጂየም አምባሰደር የሆኑት ክቡር አቶ ስቴፈን ቲጅስ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ እንዲሁም ከፍ/ቤቱ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ውይይትና የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ 

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዲስ ለሚያስገነባው የዋና...

3899

የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ.ም፡ - የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዲስ ለሚያስገነባው የዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ተክለሃይማኖት አካባቢ በሚገኘው ፍርድ ቤቱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለግንባታው በተረከበው ይዞታ ውስጥ መሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ 

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር ሰራተኞች ጉባዔ ስራውን ጀመረ

7981

የፌደራል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር ሰራተኞች ጉባዔ በደንብ ቁ 01/2015 መሠረት ተቋቁሞ ዕለተ ሰኞ ጥር 20/2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ ስብሰባውን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እና በአባላት ትውውቅ ያስጀመሩት የጉባዔው ሰብሳቢና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የጉባዔው ተመስርቶ ወደ ስራ መግባት የብዙዎች ልፋት ውጤት መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ ታሪካዊ ቀን በመብቃትችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ 

First4748495052545556Last