የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት እና የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ልዑክ ቡድን በቀን 02/05/2016 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ከ ፌደራል ፍርድ ቤቶች የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የፌደራል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር ሰራተኞች ደንብ፣ የመዋቅር ዝግጅትና የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአይ.ሲ.ቲ (ኢንፎርሜሽንና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ) ፕሮጀክቶች በሚመለከት ላይ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል፡፡